ቺሊ ውስጥ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ሲመራ

የክርስቲያናዊ ሕይወትና አገልግሎት ስብሰባ አስተዋጽኦ ታኅሣሥ 2016

የአቀራረብ ናሙናዎች

ለንቁ! መጽሔትና የመከራ መንስኤው ምን እንደሆነ ለሚገልጸው የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት የተዘጋጁ የአቀራረብ ናሙናዎች። ናሙናዎቹን ተጠቅመህ የራስህን የአቀራረብ ናሙና አዘጋጅ።

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት

‘ወደ ይሖዋ ተራራ እንውጣ’

ኢሳይያስ የጦር መሣሪያዎች ወደ ግብርና መሣሪያነት እንደሚለወጡ የገለጸ ሲሆን ይህም የይሖዋ ሕዝቦች ሰላማዊ እንደሚሆኑ ያመለክታል። (ኢሳይያስ 2:4)

ክርስቲያናዊ ሕይወት

‘ከአምላክ ፍቅር አትውጡ’ የተባለውን መጽሐፍ ስናስጠና የሰዎችን ልብ ለመንካት መጣር

“ከአምላክ ፍቅር” የተባለው መጽሐፍ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶቻችን የአምላክን መሠረታዊ ሥርዓቶች በዕለት ተለት ሕይወታቸው ተግባራዊ ማድረግ የሚችሉት እንዴት እንደሆነ እንዲገነዘቡ ይረዳቸዋል።

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት

መሲሑ ትንቢቶች እንዲፈጸሙ አድርጓል

መሲሑ በዮርዳኖስ ክልል በሚገኘው የአሕዛብ ገሊላ እንደሚሰብክ ኢሳይያስ ትንቢት ተናግሮ ነበር። ኢየሱስም በመላው ገሊላ እየተዘዋወረ ምሥራቹን በመስበክ ይህ ትንቢት እንዲፈጸም አድርጓል።

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት

“እነሆኝ! እኔን ላከኝ!”

ኢሳይያስ ያሳየውን የፈቃደኝነት መንፈስና እምነቱን መኮረጅ የምንችለው እንዴት ነው? የመንግሥቱ ሰባኪዎች ይበልጥ ወደሚያስፈልጉበት ቦታ ከተዛወረ አንድ ቤተሰብ ተሞክሮ ትምህርት መቅሰም እንችላለን።

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት

ምድር በይሖዋ እውቀት ትሞላለች

ኢሳይያስ ምድር ገነት እንደምትሆን የተናገረው ትንቢት ከዚህ በፊት፣ አሁንና ወደፊት ተፈጻሚነት የሚኖረው እንዴት ነው?

ክርስቲያናዊ ሕይወት

መለኮታዊው ትምህርት ጭፍን ጥላቻን ድል ያደርጋል

ቀደም ሲል ጠላት የነበሩ ሁለት ሰዎች አሁን ወንድማማች መሆናቸው መለኮታዊው ትምህርት አንድነት እንደሚያስገኝ ያሳያል።

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት

ሥልጣንን አላግባብ መጠቀም ሥልጣንን ያሳጣል

ሸብና ሥልጣኑን መጠቀም የነበረበት እንዴት ነበር? ይሖዋ ሸብናን በኤልያቄም የተካው ለምንድን ነው?