ክርስቲያናዊ ሕይወት
“እነሆኝ! እኔን ላከኝ!”
ኢሳይያስ ያሳየውን የፈቃደኝነት መንፈስ ልንኮርጅ ይገባል። ኢሳይያስ እምነት እንዳለው ያሳየ ሲሆን ዝርዝር ጉዳዮችን ባያውቅም እንኳ ተልዕኮውን በመቀበል ፈጣን ምላሽ ሰጥቷል። (ኢሳ 6:8) አናንተስ የመንግሥቱ ሰባኪዎች ይበልጥ ወደሚያስፈልጉበት ቦታ ሄዳችሁ ለማገልገል ስትሉ ሁኔታችሁን ማመቻቸት ትችሉ ይሆን? (መዝ 110:3) እርግጥ ‘ወጪያችሁን ማስላት’ ይኖርባችኋል። (ሉቃስ 14:27, 28) ሆኖም ለስብከቱ ሥራ ስትሉ መሥዋዕት ለመክፈል ፈቃደኛ ሁኑ። (ማቴ 8:20፤ ማር 10:28-30) ይበልጥ እርዳታ ወደሚያስፈልጋቸው ቦታዎች ሄዶ ማገልገል በተባለው ቪዲዮ ላይ ጎላ ተደርጎ እንደተገለጸው በይሖዋ አገልግሎት ስንካፈል የምናገኘው በረከት ከምንከፍለው ከየትኛውም መሥዋዕት ይበልጣል።
ቪዲዮውን ከተመለከታችሁ በኋላ በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦
-
የወንድም ዊሊያምስ ቤተሰብ አባላት ወደ ኢኳዶር ሄደው ለማገልገል ሲሉ ምን መሥዋዕቶችን ከፍለዋል?
-
ቤተሰቡ ሄደው ማገልገል የሚፈልጉበትን ቦታ ሲመርጡ የትኞቹን ነገሮች ግምት ውስጥ አስገብተዋል?
-
ምን በረከቶች አግኝተዋል?
-
የመንግሥቱ ሰባኪዎች ይበልጥ ከሚያስፈልጉበት ቦታ ጋር የተያያዙ መረጃዎችን ማግኘት የምትችሉት ከየት ነው?
በሚቀጥለው ጊዜ የቤተሰብ አምልኮ ስታደርጉ በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦
-
በቤተሰብ ደረጃ አገልግሎታችንን ማስፋት የምንችለው እንዴት ነው? (km 8/11 4-6)
-
የመንግሥቱ ሰባኪዎች ይበልጥ ወደሚያስፈልጉበት ቦታ ሄደን ማገልገል ባንችል እንኳ ያለንበትን ጉባኤ ይበልጥ መርዳት የምንችለው እንዴት ነው? (w16.03 23-25)