በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ክርስቲያናዊ ሕይወት

መለኮታዊው ትምህርት ጭፍን ጥላቻን ድል ያደርጋል

መለኮታዊው ትምህርት ጭፍን ጥላቻን ድል ያደርጋል

ይሖዋ አያዳላም። (ሥራ 10:34, 35) “ከሁሉም ብሔራት፣ ነገዶች፣ ሕዝቦችና ቋንቋዎች የተውጣጡ” ሰዎችን ይቀበላል። (ራእይ 7:9) በመሆኑም በክርስቲያን ጉባኤ ውስጥ፣ ጭፍን ጥላቻም ሆነ አድልዎ ቦታ የላቸውም። (ያዕ 2:1-4) ለመለኮታዊው ትምህርት ምስጋና ይግባውና የባሕርይ ለውጥ ባደረጉ ሰዎች በተሞላ መንፈሳዊ ገነት ውስጥ መኖር ችለናል። (ኢሳ 11:6-9) በልባችን ውስጥ ያለውን ጭፍን ጥላቻ ከሥሩ ነቅለን ለማስወገድ ከፍተኛ ጥረት ማድረጋችን አምላክን መምሰል እንደምንፈልግ ያሳያል። —ኤፌ 5:1, 2

ጆኒና ጊደየን፦ ከጠላትነት ወደ ወንድማማችነት የተባለውን ቪዲዮ ተመልከቱ። ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክሩ፦

  • አድልዎንና ጭፍን ጥላቻን በማሸነፍ ረገድ መለኮታዊው ትምህርት ሰዎች ከሚያደርጉት ጥረት የላቀ የሆነው እንዴት ነው?

  • ከዓለም አቀፉ የወንድማማች ማኅበራችን ጋር በተያያዘ በጣም የሚያስደንቅህ ነገር ምንድን ነው?

  • ክርስቲያናዊ አንድነታችንን መጠበቃችን ይሖዋን የሚያስከብረው እንዴት ነው?