በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | ኢሳይያስ 17-23

ሥልጣንን አላግባብ መጠቀም ሥልጣንን ያሳጣል

ሥልጣንን አላግባብ መጠቀም ሥልጣንን ያሳጣል

ሸብና ‘በቤቱ ላይ የተሾመ’ መጋቢ እንደነበር መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል፤ ሸብና የተሾመው በንጉሥ ሕዝቅያስ ቤት ላይ ሳይሆን አይቀርም። ከንጉሡ ቀጥሎ ያለውን ከፍተኛ ሥልጣን የያዘው እሱ ነው፤ በመሆኑም ብዙ ይጠበቅበታል

22:15, 16

  • ሸብና የይሖዋ ሕዝቦች የሚያስፈልጋቸውን ነገሮች ማሟላት ነበረበት

  • እሱ ግን ራስ ወዳድ ስለነበር ለራሱ ክብር ለማግኘት ይሯሯጥ ነበር

22:20-22

  • ይሖዋ ሸብናን በኤልያቄም ተክቶታል

  • ኤልያቄም ኃይልንና ሥልጣንን የሚያመለክተው ‘የዳዊት ቤት ቁልፍ’ ተሰጥቶታል

እስቲ የሚከተለውን አስብ፦ ሸብና ሥልጣኑን ተጠቅሞ ሌሎችን መርዳት ይችል የነበረው እንዴት ነው?