በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ክርስቲያናዊ ሕይወት

‘ከአምላክ ፍቅር አትውጡ’ የተባለውን መጽሐፍ ስናስጠና የሰዎችን ልብ ለመንካት መጣር

‘ከአምላክ ፍቅር አትውጡ’ የተባለውን መጽሐፍ ስናስጠና የሰዎችን ልብ ለመንካት መጣር

አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? ሰዎች ይሖዋን እሱ በሚፈልገው መንገድ ለማምለክ መመሪያዎቹን ማወቅና ከዚያ ጋር በሚስማማ መንገድ መኖር አለባቸው። (ኢሳ 2:3, 4) “ከአምላክ ፍቅር” የተባለው ሁለተኛው የማስጠኛ መጽሐፋችን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶቻችን የአምላክን መሠረታዊ ሥርዓቶች በዕለት ተለት ሕይወታቸው ተግባራዊ ማድረግ የሚችሉት እንዴት እንደሆነ እንዲገነዘቡ ይረዳቸዋል። (ዕብ 5:14) ጥናቶቻችን ለውጥ ለማድረግ የሚያነሳሳ ትክክለኛ ውስጣዊ ግፊት እንዲኖራቸው ከፈለግን በምናስጠናቸው ወቅት ልባቸውን ለመንካት ጥረት ማድረግ ይኖርብናል።—ሮም 6:17

ይህን ማድረግ የሚቻለው እንዴት ነው?

  • ጥናትህ የሚያስፈልጉትን ነገሮች ግምት ውስጥ አስገብተህ በሚገባ ተዘጋጅ። ስለሚማራቸው ነገሮች ያለውን ስሜት ለማወቅ የሚረዱ የአመለካከት ጥያቄዎች አዘጋጅ።—ምሳሌ 20:5be 259

  • የመጽሐፍ ቅዱስን መሠረታዊ ሥርዓቶች ተግባራዊ ማድረግ ያለውን ጥቅም ተማሪው እንዲገነዘብ ለመርዳት በመጽሐፉ ውስጥ ያሉትን ሣጥኖች ተጠቀምባቸው

  • ተማሪው ለሕሊና የተተዉ ጉዳዮችን በሚገባ እንዲገነዘብ እርዳው፤ ውሳኔ እንዳታደርግለት ግን ተጠንቀቅ።—ገላ 6:5

  • ተማሪው አንድን የመጽሐፍ ቅዱስ መሠረታዊ ሥርዓት ተግባራዊ በማድረግ ረገድ እርዳታ ያስፈልገው እንደሆነ በዘዴ ለማወቅ ሞክር። ለውጥ ለማድረግ ሊያነሳሳው የሚገባው ለይሖዋ ያለው ፍቅር እንደሆነ በደግነት ጠቁመው።—ምሳሌ 27:11፤ ዮሐ 14:31