የአቀራረብ ናሙናዎች
ንቁ!
ጥያቄ፦ ሁሉም ሰዎች ጤናማ መሆን ይፈልጋሉ ቢባል እንደምትስማማ እርግጠኛ ነኝ። ሆኖም በሽታዎችን መከላከል የምንችለው እንዴት ይመስልሃል?
ጥቅስ፦ ምሳሌ 22:3
አበርክት፦ ይህ የንቁ! መጽሔት ብልህ በመሆን በሽታን መከላከል የምንችልባቸውን መንገዶች ያብራራል።
እውነትን አስተምሩ
ጥያቄ፦ መከራ እንዲደርስብን የሚያደርገው አምላክ ነው ወይስ ሌሎች ነገሮች ናቸው?
ጥቅስ፦ ኢዮብ 34:10
እውነት፦ መከራ እንዲደርስብን ያደረገው አምላክ አይደለም። ከዚህ ይልቅ መከራ የሚያመጡብን ዲያብሎስ፣ የሰው ልጆች የሚያደርጉት መጥፎ ምርጫ እንዲሁም በአጉል ጊዜ አጉል ቦታ ላይ መገኘት ናቸው። መከራ ሲደርስብን አምላክ ይረዳናል። በእርግጥም እሱ ስለ እኛ ያስባል።
መጽሐፍ ቅዱስን መማር የሚኖርብን ለምንድን ነው? (ቪዲዮ)
ጥያቄ፦ ዓለምን የሚቆጣጠረው አምላክ ይመስልሃል? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገረው አንተ ከምታስበው የተለየ ሊሆን ይችላል። ይህ አጭር ቪዲዮ ስለዚህ ጉዳይ ያብራራል። [ቪዲዮውን አጫውት።]
አበርክት፦ ይህ መጽሐፍ፣ አምላክ መከራ እንዲኖር የፈቀደው ለምን እንደሆነና ይህን በተመለከተ የእሱ ዓላማ ምን እንደሆነ በምዕራፍ 11 ላይ ያብራራል። [የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ወይም ምን ያስተምራል የተባለውን መጽሐፍ አበርክት።]
የራስህን መግቢያ አዘጋጅ
ከላይ የተጠቀሱትን ምሳሌዎች እንደ ናሙና አድርገህ በመጠቀም በመስክ አገልግሎት ላይ የምትጠቀምበት የራስህን አቀራረብ አዘጋጅ።