ከታኅሣሥ 17-23
የሐዋርያት ሥራ 15-16
መዝሙር 96 እና ጸሎት
የመግቢያ ሐሳብ (3 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት
“በአምላክ ቃል ላይ ተመሥርተው በአንድ ልብ ወሰኑ”፦ (10 ደቂቃ)
ሥራ 15:1, 2—ከግርዘት ጋር በተያያዘ በተፈጠረው ውዝግብ የተነሳ የጥንቱ የክርስቲያን ጉባኤ ሊከፋፈል ነበር (bt 102-103 አን. 8)
ሥራ 15:13-20—የበላይ አካሉ በቅዱሳን መጻሕፍት ላይ የተመሠረተ ውሳኔ አደረገ (w12 1/15 5 አን. 6-7)
ሥራ 15:28, 29፤ 16:4, 5—የበላይ አካሉ ያደረገው ውሳኔ ጉባኤዎቹን አጠናከራቸው (bt 123 አን. 18)
መንፈሳዊ ዕንቁዎችን በምርምር ማግኘት፦ (8 ደቂቃ)
ሥራ 16:6-9—አገልግሎታችንን ከማስፋት ጋር በተያያዘ ይህ ዘገባ ምን ያስተምረናል? (w12 1/15 10 አን. 8)
ሥራ 16:37—ሐዋርያው ጳውሎስ የሮም ዜግነት ያለው መሆኑ ምሥራቹን ለማስፋፋት የረዳው እንዴት ነው? (nwtsty ለጥናት የሚረዳ መረጃ)
ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ስለ ይሖዋ ምን ትምህርት አግኝታችኋል?
ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ምን ሌሎች መንፈሳዊ ዕንቁዎች አግኝታችኋል?
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች) ሥራ 16:25-40
በአገልግሎት ውጤታማ ለመሆን ተጣጣር
መመሥከር፦ (2 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች) በውይይት ናሙናው ጀምር። በክልላችሁ ለተለመደ የተቃውሞ ሐሳብ ምላሽ ስጥ።
የመጀመሪያው ተመላልሶ መጠየቅ፦ (3 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች) የውይይት ናሙናውን ተጠቀም። መጽሐፍ ቅዱስን መማር የሚኖርብን ለምንድን ነው? የተባለውን ቪዲዮ አስተዋውቅና ተወያዩበት። (ክፍሉ ላይ ቪዲዮውን ማጫወት አያስፈልግህም።)
ሁለተኛው ተመላልሶ መጠየቅ—ቪዲዮ፦ (5 ደቂቃ) ቪዲዮውን አጫውትና ተወያዩበት።
ክርስቲያናዊ ሕይወት
“ለይሖዋ የውዳሴ መዝሙር በደስታ ዘምሩ”፦ (15 ደቂቃ) በውይይት የሚቀርብ። ልጆች ይሖዋን በመዝሙር ያወድሳሉ የሚለውን ቪዲዮ አጫውት። ክፍልህን ስትደመድም፣ አድማጮችህ በሙሉ ተነስተው መዝሙር 084 እገዛ የሚያስፈልጋቸውን መርዳት የተባለውን ቪዲዮ ሲዘመር አብረው እንዲዘምሩ ጋብዝ።
የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦ (30 ደቂቃ) jy ምዕ. 39
ክለሳና የቀጣዩ ሳምንት ማስተዋወቂያ (3 ደቂቃ)
መዝሙር 120 እና ጸሎት