በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ክርስቲያናዊ ሕይወት

ለይሖዋ የውዳሴ መዝሙር በደስታ ዘምሩ

ለይሖዋ የውዳሴ መዝሙር በደስታ ዘምሩ

ጳውሎስና ሲላስ እስር ቤት ውስጥ እያሉ ይሖዋን በመዝሙር ያወድሱ ነበር። (ሥራ 16:25) መዝሙር መዘመራቸው ለመጽናት እንደረዳቸው ጥርጥር የለውም። በዛሬው ጊዜ ያለን ክርስቲያኖችስ? ለአምልኮ የምንጠቀምባቸው መዝሙሮችና የይሖዋ ድርጅት ያዘጋጀልን ሌሎች ሙዚቃዎች መንፈሳችንን ያድሱልናል እንዲሁም ፈተናዎችን በታማኝነት እንድንወጣ ይረዱናል። ከሁሉ በላይ ደግሞ ይሖዋን ለማወደስ ያስችሉናል። (መዝ 28:7) ከመዝሙሮቻችን መካከል ቢያንስ የአንዳንዶቹን ግጥሞች በቃላችን እንድንይዝ ማበረታቻ ተሰጥቶናል። በዚህ ረገድ ጥረት እያደረግክ ነው? በቤተሰብ አምልኮ ፕሮግራማችን ላይ መዝሙሮቹን መለማመድና ግጥሞቻቸውን ማጥናት እንችላለን።

ልጆች ይሖዋን በመዝሙር ያወድሳሉ የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦

  • የመንግሥቱ መዝሙሮች ምን በጎ ተጽዕኖ ያሳድሩብናል?

  • የኦዲዮ/ቪዲዮ ክፍል አንድን መዝሙር ለመቅዳት ዝግጅት የሚያደርገው እንዴት ነው?

  • የሚቀዱት ልጆች ከቤተሰባቸው ጋር ሆነው የሚለማመዱት እንዴት ነው?

  • በጣም የምትወዳቸው መዝሙሮች የትኞቹ ናቸው? ለምንስ?