በአምላክ ቃል ላይ ተመሥርተው በአንድ ልብ ወሰኑ
ይህ ጉዳይ እልባት ካገኘበት መንገድ ምን ትምህርት እናገኛለን?
15:1, 2—ትሕትናና ትዕግሥት ማሳየት። ጳውሎስና በርናባስ ጉዳዩን በራሳቸው መንገድ ከመፍታት ይልቅ ከይሖዋ ድርጅት መመሪያ ለማግኘት ጥረት አድርገዋል።
15:28, 29—በአምላክ ድርጅት መታመን። በአንጾኪያ ያለው ጉባኤ ይሖዋ በመንፈስ ቅዱስና በክርስቶስ ኢየሱስ አማካኝነት መመሪያ እንደሚሰጥ ተማምኖ ነበር።
16:4, 5—መታዘዝ። ጉባኤዎቹ የበላይ አካሉ የላከውን መመሪያ ሲከተሉ እየተጠናከሩና በቁጥር እየጨመሩ ሄዱ።