ክርስቲያናዊ ሕይወት
በአገልግሎት ረገድ ክህሎታችንን ማዳበር—“ትክክለኛ የልብ ዝንባሌ ያላቸው” ሰዎች ደቀ መዛሙርት እንዲሆኑ መርዳት
አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? ይሖዋ የእውነት ዘር “ትክክለኛ የልብ ዝንባሌ” ባላቸው ሰዎች ልብ ውስጥ እንዲያድግ ያደርጋል። (ሥራ 13:48፤ 1ቆሮ 3:7) እኛም አገልግሎታችንን ስናከናውን፣ የተማሩትን ነገር በተግባር ማዋል በሚፈልጉ ሰዎች ላይ ትኩረት በማድረግ ከይሖዋ ጋር አብረን መሥራት እንችላለን። (1ቆሮ 9:26) የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶቻችን መዳን ለማግኘት፣ ተጠምቀው ክርስቲያን መሆን እንዳለባቸው ማወቅ ይኖርባቸዋል። (1ጴጥ 3:21) የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶቻችንን በሕይወታቸው ውስጥ ለውጥ እንዲያደርጉ፣ ምሥራቹን እንዲሰብኩና ሰዎችን እንዲያስተምሩ ብሎም ሕይወታቸውን ለይሖዋ እንዲወስኑ በማስተማር ደቀ መዛሙርት እንዲሆኑ መርዳት እንችላለን።—ማቴ 28:19, 20
ይህን ማድረግ የሚቻለው እንዴት ነው?
-
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶቻችሁን የምታስጠኗቸው፣ ይሖዋን “ማወቅ” እና እሱን በሚያስደስት መንገድ መኖር እንዲችሉ ለመርዳት እንደሆነ አስታውሷቸው።—ዮሐ 17:3
-
መንፈሳዊ እድገት እንዳያደርጉ እንቅፋት የሚሆኑባቸውን ነገሮች እንዲያሸንፉ ለምሳሌ መጥፎ ልማዶችን እንዲያስወግዱ እንዲሁም ጥሩ ካልሆኑ ጓደኞች እንዲርቁ እርዷቸው።
-
ከመጠመቃቸው በፊትም ሆነ ከተጠመቁ በኋላ አበረታቷቸው እንዲሁም አጠናክሯቸው።—ሥራ 14:22
ይሖዋ አምላክ ይረዳችኋል የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦
-
አንድ ሰው ራሱን ወስኖ ከመጠመቅ ወደኋላ የሚለው የትኞቹን ነገሮች በመፍራት ሊሆን ይችላል?
-
ሽማግሌዎች የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች እድገት እንዲያደርጉ መርዳት የሚችሉት እንዴት ነው?
-
ኢሳይያስ 41:10 ስለ ይሖዋ ምን ያስተምረናል?
-
ፍጹማን ባንሆንም ይሖዋን እሱ በሚፈልገው መንገድ ለማገልገል የሚረዱን የትኞቹ ነገሮች ናቸው?