በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ከታኅሣሥ 24-30

የሐዋርያት ሥራ 17-18

ከታኅሣሥ 24-30
  • መዝሙር 78 እና ጸሎት

  • የመግቢያ ሐሳብ (3 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት

  • በመስበክና በማስተማር ረገድ የሐዋርያው ጳውሎስን ምሳሌ ተከተሉ”፦ (10 ደቂቃ)

    • ሥራ 17:2, 3—ጳውሎስ አድማጮቹን ከቅዱሳን መጻሕፍት እየጠቀሰ ያወያያቸው እንዲሁም ለሚያስተምረው ነገር ማስረጃ ያቀርብ ነበር (nwtsty ለጥናት የሚረዱ መረጃዎች)

    • ሥራ 17:17—ጳውሎስ ሰዎችን በሚያገኝበት ቦታ ሁሉ ይሰብክ ነበር (nwtsty ለጥናት የሚረዳ መረጃ)

    • ሥራ 17:22, 23—ጳውሎስ በአካባቢው ያሉትን ነገሮች ያስተውል እንዲሁም ከአድማጮቹ ጋር የሚያግባባውን ሐሳብ ይጠቅስ ነበር (nwtsty ለጥናት የሚረዳ መረጃ)

  • መንፈሳዊ ዕንቁዎችን በምርምር ማግኘት፦ (8 ደቂቃ)

    • ሥራ 18:18—ጳውሎስ የተሳለው ስእለት ምን ነበር? (w08 5/15 32 አን. 5)

    • ሥራ 18:21—መንፈሳዊ ግቦች ላይ ለመድረስ ስንጣጣር የጳውሎስን ምሳሌ መከተል የምንችለው እንዴት ነው? (nwtsty ለጥናት የሚረዳ መረጃ)

    • ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ስለ ይሖዋ ምን ትምህርት አግኝታችኋል?

    • ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ምን ሌሎች መንፈሳዊ ዕንቁዎች አግኝታችኋል?

  • የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች) ሥራ 17:1-15

በአገልግሎት ውጤታማ ለመሆን ተጣጣር

  • ሁለተኛው ተመላልሶ መጠየቅ፦ (3 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች) የውይይት ናሙናውን ተጠቀም። መጽሐፍ ቅዱስን የምናስጠናው እንዴት ነው? የተባለውን ቪዲዮ አስተዋውቅና ተወያዩበት።

  • ሦስተኛው ተመላልሶ መጠየቅ፦ (3 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች) በሁለተኛው ተመላልሶ መጠየቅ ላይ ላነሳኸው ጥያቄ መልስ ለመስጠት የሚያስችል ጥቅስ መርጠህ ተጠቀም፤ ከዚያም አንድ የማስጠኛ ጽሑፍ አበርክት።

  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦ (6 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች) jl ትምህርት 7

ክርስቲያናዊ ሕይወት

  • መዝሙር 70

  • ምሥራቹን በተሟላ ሁኔታ ስበኩ እንዲሁም አስተምሩ፦ (15 ደቂቃ) በውይይት የሚቀርብ። የቤተሰብ አምልኮ፦ ጳውሎስ ምሥራቹን በተሟላ ሁኔታ ሰብኳል የሚለውን ቪዲዮ አጫውት። ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ጠይቅ፦ በቪዲዮው ላይ የሚታየው ቤተሰብ አባላት የአገልግሎታቸውን ጥራት ለማሻሻል ምን ማድረግ እንደሚያስፈልጋቸው ተገንዝበዋል? ሐዋርያው ጳውሎስ አገልግሎቱን ያከናወነበትን መንገድ በመመልከት በየትኞቹ አቅጣጫዎች ምሳሌውን ለመከተል ጥረት አድርገዋል? ይህን ማድረጋቸው ምን በረከት አስገኝቶላቸዋል? በቤተሰብ አምልኮ ፕሮግራማችሁ ላይ የትኞቹን ነገሮች ማካተት ትችላላችሁ?

  • የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦ (30 ደቂቃ) jy ምዕ. 40

  • ክለሳና የቀጣዩ ሳምንት ማስተዋወቂያ (3 ደቂቃ)

  • መዝሙር 106 እና ጸሎት