በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | የሐዋርያት ሥራ 9-11

ቀንደኛ አሳዳጅ የነበረው ሰው ቀናተኛ ክርስቲያን ሆነ

ቀንደኛ አሳዳጅ የነበረው ሰው ቀናተኛ ክርስቲያን ሆነ

9:15, 16, 20-22

ሳኦል ስለ ኢየሱስ ካወቀ በኋላ ወዲያውኑ እርምጃ ወስዷል። ሳኦል ከሌሎች አይሁዳውያን የተለየ አቋም የወሰደው ለምንድን ነው? ከሰው ይልቅ አምላክን ስለፈራ እንዲሁም ክርስቶስ ላሳየው ምሕረት ጥልቅ አድናቆት ስለነበረው ነው። አንተም መጽሐፍ ቅዱስን እያጠናህ ቢሆንም ራስህን ወስነህ አልተጠመቅክ ይሆናል፤ ታዲያ ባወቅከው ነገር ላይ ተመሥርተህ ቆራጥ እርምጃ በመውሰድ የሳኦልን ምሳሌ ትከተላለህ?