ከታኅሣሥ 31, 2018–ጥር 6, 2019
የሐዋርያት ሥራ 19-20
መዝሙር 103 እና ጸሎት
የመግቢያ ሐሳብ (3 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት
“ለራሳችሁም ሆነ ለመንጋው ሁሉ ትኩረት ስጡ”፦ (10 ደቂቃ)
ሥራ 20:28—ሽማግሌዎች ለጉባኤው እረኛ ሆነው ያገለግላሉ (w11 6/15 20-21 አን. 5)
ሥራ 20:31—ሽማግሌዎች እንደ አስፈላጊነቱ “ሌሊትና ቀን” መንጋውን ይረዳሉ (w13 1/15 31 አን. 15)
ሥራ 20:35—ሽማግሌዎች የራሳቸውን ጥቅም የመሠዋት መንፈስ ሊኖራቸው ይገባል (bt 172 አን. 20)
መንፈሳዊ ዕንቁዎችን በምርምር ማግኘት፦ (8 ደቂቃ)
ሥራ 19:9—ሐዋርያው ጳውሎስ በትጋት በመሥራትና እንደ ሁኔታው ማስተካከያ በማድረግ ረገድ ምን ምሳሌ ትቷል? (bt 161 አን. 11)
ሥራ 19:19—የኤፌሶን ክርስቲያኖች ጥሩ ምሳሌ የተዉት እንዴት ነው? (bt 162-163 አን. 15)
ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ስለ ይሖዋ ምን ትምህርት አግኝታችኋል?
ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ምን ሌሎች መንፈሳዊ ዕንቁዎች አግኝታችኋል?
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች) ሥራ 19:1-20
በአገልግሎት ውጤታማ ለመሆን ተጣጣር
ሁለተኛው ተመላልሶ መጠየቅ፦ (3 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች) በውይይት ናሙናው ጀምር። ለምታነጋግረው ሰው የJW.ORG አድራሻ ካርድ ስጥ።
ሦስተኛው ተመላልሶ መጠየቅ፦ (3 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች) በሁለተኛው ተመላልሶ መጠየቅ ላይ ላነሳኸው ጥያቄ መልስ ለመስጠት የሚያስችል ጥቅስ መርጠህ ተጠቀም፤ ከዚያም ለቀጣዩ ተመላልሶ መጠየቅ ያዘጋጀኸውን ጥያቄ ጠይቀው።
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦ (6 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች) jl ትምህርት 15
ክርስቲያናዊ ሕይወት
ለመልካም ሥራ የሚጣጣሩ ወጣት ወንዶችን አሠልጥኑ፦ (15 ደቂቃ) በውይይት የሚቀርብ። ቪዲዮውን አጫውት። ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ጠይቅ፦ ሽማግሌዎች በጉባኤ ውስጥ ምን ጠቃሚ ድርሻ አላቸው? (ሥራ 20:28) ሽማግሌዎች ሌሎችን ማሠልጠናቸውን መቀጠል ያለባቸው ለምንድን ነው? ሽማግሌዎች፣ ኢየሱስ ሐዋርያቱን ያሠለጠነበትን መንገድ በማስተዋል ምሳሌውን መከተል የሚችሉት እንዴት ነው? ወንድሞች ሥልጠና ማግኘትን በተመለከተ ምን አመለካከት ሊኖራቸው ይገባል? (ሥራ 20:35፤ 1ጢሞ 3:1) ሽማግሌዎች ለሌሎች ወንድሞች ምን ጠቃሚ ሥልጠና መስጠት ይችላሉ? ሽማግሌዎች የሚያሠለጥኗቸውን ወንድሞች በተመለከተ ምን ዓይነት ሚዛናዊ አመለካከት ሊኖራቸው ይገባል?
የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦ (30 ደቂቃ) jy ምዕ. 41
ክለሳና የቀጣዩ ሳምንት ማስተዋወቂያ (3 ደቂቃ)
መዝሙር 32 እና ጸሎት