አንድም ሰው ሊቆጥራቸው የማይችል እጅግ ብዙ ሕዝብ የይሖዋን በረከት አገኙ
ይሖዋ የእጅግ ብዙ ሕዝብ አባላትን የሚባርካቸው ለምንድን ነው?
-
‘በይሖዋ ዙፋን ፊት ቆመዋል’፤ ይህም የይሖዋን ሉዓላዊነት ሙሉ በሙሉ እንደሚደግፉ ያሳያል
-
‘ነጭ ልብስ ለብሰዋል’፤ ይህም በክርስቶስ መሥዋዕት ላይ ባላቸው እምነት አማካኝነት በይሖዋ ፊት ንጹሕና ጻድቅ ተደርገው እንደሚታዩ ያሳያል
-
‘ቀንና ሌሊት ቅዱስ አገልግሎት ያቀርባሉ’፤ ይህም ለይሖዋ የማይቋረጥና ከልብ የመነጨ አምልኮ ለማቅረብ ጥረት እንደሚያደርጉ ያሳያል
የእጅግ ብዙ ሕዝብ አባል ለመሆን ምን ማድረግ ይኖርብኛል?