በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ክርስቲያናዊ ሕይወት

በአገልግሎት ረገድ ክህሎታችንን ማዳበር—እንደ ሁኔታው ማስተካከያ ማድረግ

በአገልግሎት ረገድ ክህሎታችንን ማዳበር—እንደ ሁኔታው ማስተካከያ ማድረግ

አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? ቅቡዓኑና ሌሎች በጎች፣ ሁሉም ዓይነት ሰዎች ‘የሕይወትን ውኃ በነፃ እንዲወስዱ’ እየጋበዙ ነው። (ራእይ 22:17) ይህ ምሳሌያዊ ውኃ ይሖዋ ታዛዥ የሆኑ ሰዎችን ከኃጢአትና ከሞት ለማላቀቅ ያደረጋቸውን ዝግጅቶች በሙሉ ያመለክታል። የተለያየ ባሕልና ሃይማኖት ያላቸውን ሰዎች ለመርዳት ‘የዘላለሙን ምሥራች’ እነሱን በግለሰብ ደረጃ ሊማርካቸው በሚችል መንገድ ማቅረብ ይኖርብናል።—ራእይ 14:6

ይህን ማድረግ የሚቻለው እንዴት ነው?

  • በክልልህ ውስጥ ያሉትን ሰዎች ልብ ሊነኩ የሚችሉ ርዕሰ ጉዳዮችና ጥቅሶች ምረጥ። በውይይት ናሙናዎች ላይ የወጣ አንድ መግቢያ ወይም ከዚህ በፊት ውጤታማ ሆኖ ያገኘኸውን ሌላ ርዕሰ ጉዳይ መጠቀም ትችላለህ። የሰዎችን ትኩረት የሚስቡት የትኞቹ ርዕሰ ጉዳዮችና ጥቅሶች ናቸው? የብዙ ሰዎች መነጋገሪያ የሆነ በቅርቡ የወጣ ዜና አለ? የወንዶችን ትኩረት የሚስበውና የሴቶችን ትኩረት የሚስበው የትኛው ርዕሰ ጉዳይ ነው?

  • መግቢያህን ተጠቅመህ ሰዎችን ስታነጋግር በአካባቢህ የተለመዱ ሰላምታዎችን አካትት፤ እንዲሁም ባህላቸውን ግምት ውስጥ አስገባ።—2 ቆሮ 6:3, 4

  • በማስተማሪያ መሣሪያዎቻችን ውስጥ ካሉት ጽሑፎችና ቪዲዮዎች ጋር በሚገባ ተዋወቅ፤ ይህም ፍላጎት ያለው ሰው ስታገኝ እንድትጠቀምባቸው ያስችልሃል

  • በክልልህ ውስጥ የምታገኛቸው ሰዎች በሚናገሯቸው ቋንቋዎች የተዘጋጁ ጽሑፎችንና ቪዲዮዎችን አውርድ

  • የምታነጋግረውን ሰው ግምት ውስጥ በማስገባት በርዕሰ ጉዳዩ ላይ እንደ ሁኔታው ማስተካከያ አድርግ። (1ቆሮ 9:19-23) ለምሳሌ የምታነጋግረው ሰው የሚወደውን ሰው በቅርቡ በሞት እንዳጣ ቢነግርህ ምን ትላለህ?

ቪዲዮውን ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦

  • አስፋፊው ከቤቱ ባለቤት ጋር ውይይት ለመጀመር የትኛውን ርዕሰ ጉዳይ አንስቷል?

  • የቤቱ ባለቤት በሕይወቱ ውስጥ ምን አጋጥሞታል?

  • ለዚህ ሁኔታ ይበልጥ ተስማሚ የሆነው የትኛው ጥቅስ ነው? ለምንስ?

  • በክልልህ ውስጥ የምታገኛቸውን ሰዎች ትኩረት ለመሳብ በመግቢያህ ላይ ማስተካከያ ማድረግ የምትችለው እንዴት ነው?