ከስርየት ቀን ምን ትምህርት እናገኛለን?
በስርየት ቀን ዕጣን የሚጨስ መሆኑ ምን ያስተምረናል?
-
የይሖዋ ታማኝ አገልጋዮች የሚያቀርቡት ጸሎት በዕጣን ተመስሏል። (መዝ 141:2) ሊቀ ካህናቱ፣ ዕጣኑን ይዞ ወደ ይሖዋ ፊት የሚገባው በታላቅ አክብሮት እንደሆነ ሁሉ እኛም በጸሎት ወደ ይሖዋ የምንቀርበው በጥልቅ አክብሮት መሆን ይኖርበታል
-
ሊቀ ካህናቱ መሥዋዕቶቹን ከማቅረቡ በፊት ዕጣኑን ማጨስ ነበረበት። በተመሳሳይም ኢየሱስ ሕይወቱን መሥዋዕት አድርጎ ከማቅረቡ በፊት፣ መሥዋዕቱ በይሖዋ ዘንድ ተቀባይነት እንዲያገኝ ማድረግ ይጠበቅበት ነበር፤ ይህም በምድር ላይ ባሳለፈው ሕይወት በሙሉ ንጹሕ አቋሙን መጠበቅና በታማኝነት መመላለስ ይጠይቅበት ነበር
የማቀርበው መሥዋዕት በይሖዋ ዘንድ ተቀባይነት እንዲኖረው ማድረግ የምችለው እንዴት ነው?