በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ክርስቲያናዊ ሕይወት

ይሖዋ ተግሣጽ የሚሰጥበትን መንገድ በመደገፍ ፍቅር እናሳያለን

ይሖዋ ተግሣጽ የሚሰጥበትን መንገድ በመደገፍ ፍቅር እናሳያለን

ውገዳ ለጉባኤው ጥበቃ ይሆናል፤ ንስሐ ለመግባት ፈቃደኛ ያልሆነው ሰውም ተገቢውን ተግሣጽ እንዲያገኝ ያደርጋል። (1ቆሮ 5:6, 11) ይሖዋ ተግሣጽ የሚሰጥበትን ይህን ዝግጅት የምንደግፍ ከሆነ ፍቅር እናሳያለን። ውገዳ የቅርብ የቤተሰብ አባላትንና የፍርድ ኮሚቴውን አባላት ጨምሮ ጉዳዩ በሚመለከታቸው ሰዎች ሁሉ ላይ ሐዘን ሊያስከትል ይችላል፤ በዚህ ጊዜም ዝግጅቱን መደገፋችን ፍቅራችንን የሚያሳየው እንዴት ነው?

ከሁሉ በላይ፣ ለይሖዋ ስምና ለቅድስና መሥፈርቱ ፍቅር እንዳለን ያሳያል። (1ጴጥ 1:14-16) ለተወገደው ሰው ያለንን ፍቅርም ያሳያል። ጠንከር ያለ ተግሣጽ ሐዘን የሚያስከትል ቢሆንም ግለሰቡ “የጽድቅን ሰላማዊ ፍሬ” እንዲያፈራ ሊያደርገው ይችላል። (ዕብ 12:5, 6, 11) ከተወገደ ወይም ራሱን ካገለለ ሰው ጋር ያለንን ግንኙነት ከቀጠልን ይሖዋ ለሚሰጠው ተግሣጽ እንቅፋት እንሆናለን። ይሖዋ ሕዝቡን የሚገሥጸው “በተገቢው መጠን” እንደሆነ አስታውሱ። (ኤር 30:11) ግለሰቡ ወደ መሐሪው አባታችን እንደሚመለስ ተስፋ እናደርጋለን፤ እስከዚያው ግን ይሖዋ የሚሰጠውን ተግሣጽ እንደግፍ እንዲሁም መንፈሳዊ ልማዳችንን ይዘን እንቀጥል።—ኢሳ 1:16-18፤ 55:7

ባልተከፋፈለ ልብ ታማኝነትን ጠብቁ የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦

  • ክርስቲያን ወላጆች፣ ልጃቸው ይሖዋን ሲተው ምን ይሰማቸዋል?

  • ጉባኤው፣ ታማኝ የሆኑትን የቤተሰብ አባላት መደገፍ የሚችለው እንዴት ነው?

  • ለይሖዋ ያለን ታማኝነት፣ ለቤተሰባችን ካለን ታማኝነት ሊበልጥ እንደሚገባ የሚያጎላው የትኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ዘገባ ነው?

  • ከቤተሰባችን ይልቅ ለይሖዋ ታማኝ እንደሆንን ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው?