በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ክርስቲያናዊ ሕይወት

እህቶች ተጨማሪ ነገር ለማከናወን መጣጣር የሚችሉት እንዴት ነው?

እህቶች ተጨማሪ ነገር ለማከናወን መጣጣር የሚችሉት እንዴት ነው?

እህቶች ከመንግሥቱ ሥራ ጋር በተያያዘ ጉልህ አስተዋጽኦ ያበረክታሉ። (መዝ 68:11) ብዙዎቹን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች የሚመሩት እንዲሁም ከዘወትር አቅኚዎች መካከል አብላጫውን ቦታ የሚይዙት እህቶች ናቸው። በሺዎች የሚቆጠሩ ታታሪ እህቶቻችን ቤቴላውያን፣ ሚስዮናውያን፣ የግንባታ አገልጋዮችና ተርጓሚዎች ሆነው ያገለግላሉ። የጎለመሱ እህቶች ቤተሰባቸውንና ጉባኤያቸውን ያንጻሉ። (ምሳሌ 14:1) እህቶች ሽማግሌዎች ወይም የጉባኤ አገልጋዮች ሆነው ማገልገል ባይችሉም በጉባኤው ውስጥ ሊያወጧቸው የሚችሏቸው ግቦች አሉ። እህት ከሆንሽ፣ በጉባኤው ውስጥ የትኞቹን ግቦች ማውጣት ትችያለሽ?

  • ክርስቲያናዊ ባሕርያትን ማዳበር።—1ጢሞ 3:11፤ 1ጴጥ 3:3-6

  • በጉባኤው ውስጥ ብዙ ተሞክሮ የሌላቸውን እህቶች መርዳት።—ቲቶ 2:3-5

  • የአገልግሎት ጥራትሽን ማሻሻል እንዲሁም በአገልግሎት የምታደርጊውን ተሳትፎ ማሳደግ

  • ሌላ ቋንቋ መማር

  • ሰባኪዎች ይበልጥ ወደሚያስፈልጉበት ቦታ መዛወር

  • በቤቴል ለማገልገል ወይም በቲኦክራሲያዊ ሕንፃዎች ግንባታ ላይ እገዛ ለማበርከት ማመልከት

  • በመንግሥቱ ወንጌላውያን ትምህርት ቤት ለመማር ማመልከት

‘በጌታ ሆነው በትጋት የሚሠሩ ሴቶች’ የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተለውን ጥያቄ ለመመለስ ሞክር፦

  • እህቶች ከሰጡት ሐሳብ ምን ማበረታቻ አግኝታችኋል?