በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ክርስቲያናዊ ሕይወት

የዚህን ሥርዓት መጨረሻ በልበ ሙሉነት ተጠባበቁ

የዚህን ሥርዓት መጨረሻ በልበ ሙሉነት ተጠባበቁ

በቅርቡ፣ ይሖዋ ለዚህ ዓለም የሚያሳየው ትዕግሥት ያልቃል። የሐሰት ሃይማኖት ይጠፋል፤ ግንባር የፈጠሩ ብሔራት በአምላክ ሕዝቦች ላይ ጥቃት ይሰነዝራሉ፤ እንዲሁም ይሖዋ በአርማጌዶን ክፉዎችን ያጠፋል። ክርስቲያኖች እነዚህን አስደናቂ ክንውኖች በጉጉት ይጠባበቃሉ።

እርግጥ ነው፣ ስለ ታላቁ መከራ የማናውቃቸው ዝርዝር ጉዳዮች አሉ። ለምሳሌ የሚጀምርበትን ትክክለኛ ጊዜ አናውቅም። የፖለቲካ ኃይሎች በሃይማኖቶች ላይ ጥቃት ለመሰንዘር የሚጠቀሙበትን ሰበብ አናውቅም። ብሔራት በአምላክ ሕዝቦች ላይ የሚሰነዝሩት ጥቃት ለምን ያህል ጊዜ እንደሚቆይ እንዲሁም የትኞቹን ነገሮች እንደሚያካትት አናውቅም። በተጨማሪም ይሖዋ በአርማጌዶን ክፉዎችን ለማጥፋት የሚጠቀምበትን ዘዴ በእርግጠኝነት አናውቅም።

ይሁንና መጽሐፍ ቅዱስ የወደፊቱን ጊዜ በድፍረትና በልበ ሙሉነት ለመጠባበቅ የሚያስፈልጉንን መረጃዎች በሙሉ ይሰጠናል። ለምሳሌ የምንኖረው “በመጨረሻዎቹ ቀናት” መጨረሻ እንደሆነ እናውቃለን። (2ጢሞ 3:1) እውነተኛው ሃይማኖት እንዳይጠፋ ሲባል በሃይማኖቶች ላይ የሚሰነዘረው ጥቃት ‘እንደሚያጥር’ እናውቃለን። (ማቴ 24:22) ይሖዋ ሕዝቦቹን እንደሚያድን እናውቃለን። (2ጴጥ 2:9) በተጨማሪም ይሖዋ ክፉዎችን ለማጥፋትና እጅግ ብዙ ሕዝብን ከአርማጌዶን ለማሻገር የሚጠቀምበት መሪ ጻድቅና ኃያል እንደሆነ እናውቃለን።—ራእይ 19:11, 15, 16

ወደፊት የሚመጡት ክንውኖች፣ ሰዎች ‘ከፍርሃት የተነሳ እንዲዝለፈለፉ’ እንደሚያደርጓቸው ጥያቄ የለውም። ይሁንና ይሖዋ በጥንት ጊዜ ሕዝቦቹን ስላዳነበት መንገድ እንዲሁም ስለ ወደፊቱ ጊዜ የነገረንን ነገር ካነበብንና ካሰላሰልን መዳናችን እየቀረበ እንደሆነ ተማምነን ‘ቀጥ ብለን መቆምና ራሳችንን ቀና ማድረግ’ እንችላለን።—ሉቃስ 21:26, 28