ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት
የይሖዋ ትዕግሥት ገደብ አለው
ይሖዋ አሦር እስራኤልን ድል እንድታደርግ ፈቀደ (2ነገ 17:5, 6፤ w05 11/15 29 አን. 16)
ይሖዋ ሕዝቦቹ በተደጋጋሚ ስላስቆጡት ቀጣቸው (2ነገ 17:9-12፤ w12 4/1 10 አን. 2፤ w01 11/1 10 አን. 10)
ይሖዋ እስራኤላውያንን በትዕግሥት ይዟቸዋል፤ እንዲሁም በተደጋጋሚ አስጠንቅቋቸዋል (2ነገ 17:13, 14)
አፍቃሪ የሆነው የሰማዩ አባታችን ፍጹማን ያልሆኑ ሰዎችን የሚይዘው በትዕግሥት ነው። (2ጴጥ 3:9) ሆኖም ዓላማውን ለመፈጸም ሲል በቅርቡ ክፉዎችን ለማጥፋት እርምጃ ይወስዳል። ይህን ማወቃችን ተግሣጽ ለመቀበልና በጥድፊያ ስሜት ለመስበክ የሚያነሳሳን እንዴት ነው?