በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ክርስቲያናዊ ሕይወት

ስደት ሲደርስባችሁ ደስ ይበላችሁ

ስደት ሲደርስባችሁ ደስ ይበላችሁ

ክርስቲያኖች ስደት እንደሚደርስባቸው ይጠብቃሉ። (ዮሐ 15:20) ስደት በተወሰነ መጠን ጭንቀት፣ አንዳንዴም ሥቃይ ሊያስከትል ቢችልም በጽናት ስንቋቋመው ደስታ እናገኛለን።—ማቴ 5:10-12፤ 1ጴጥ 2:19, 20

ምንም ነገር ደስታችሁን እንዲያሳጣችሁ አትፍቀዱ—ስደት የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦

የሚከተሉት ነገሮች ያላቸውን ጥቅም በተመለከተ ከወንድም ባዤኖቭ ተሞክሮ ምን ትምህርት አግኝተሃል?

  • መጽሐፍ ቅዱስን በየዕለቱ ማንበብ

  • ከእምነት ባልንጀሮቻችን ድጋፍ ማግኘት a

  • አዘውትሮ መጸለይ

  • የመንግሥቱን መዝሙሮች መዘመር

  • ስለ እምነታችን መናገር

a ስለታሰሩ ክርስቲያኖች መጸለይ እንችላለን፤ እንዲያውም በጸሎታችን ላይ ስማቸውን መጥቀስ እንችላለን። ይሁንና ወደ እነሱ መላክ የምንፈልገውን የግል ደብዳቤ ቅርንጫፍ ቢሮው ሊያደርስልን አይችልም።