ክርስቲያናዊ ሕይወት
ጸሎታችን በይሖዋ ዘንድ ውድ ነው
ተቀባይነት ያላቸው ጸሎቶች፣ ዘወትር በቤተ መቅደሱ በይሖዋ ፊት በሚጨሰው ጣፋጭ መዓዛ ያለው ዕጣን ተመስለዋል። (መዝ 141:2) ለሰማዩ አባታችን ፍቅራችንንና አድናቆታችንን ስንገልጽለት፣ ስለሚያስጨንቁንና ስለምንፈልጋቸው ነገሮች ስንነግረው እንዲሁም አመራር እንዲሰጠን ስንጠይቀው ከእሱ ጋር ያለንን ወዳጅነት ከፍ አድርገን እንደምንመለከተው እናሳያለን። እርግጥ ይሖዋ በስብሰባዎቻችን ላይ በሕዝብ ፊት የሚቀርቡትን አጭር ጸሎቶች ወሳኝ የአምልኳችን ክፍል አድርጎ ይመለከታቸዋል። ይሁንና በግላችን በምንጸልይበት ጊዜ ልባችንን አፍስሰን ለረጅም ሰዓት ስናነጋግረው ይሖዋ ይበልጥ ይደሰታል!—ምሳሌ 15:8
ለጸሎት ትልቅ ቦታ እሰጣለሁ የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦
-
ወንድም ጆንሰን የትኞቹን የአገልግሎት መብቶች አግኝቷል?
-
ወንድም ጆንሰን በጸሎት አማካኝነት በይሖዋ እንደሚታመን ያሳየው እንዴት ነው?
-
ከወንድም ጆንሰን ተሞክሮዎች ምን ትምህርት አግኝተሃል?