ክርስቲያናዊ ሕይወት
ይሖዋ በትጋት የምናከናውነውን ሥራ አይረሳም
አንዳንድ ጊዜ ሌሎች እነሱን ለመርዳት በትጋት የምናከናውነውን ሥራ እንደማያደንቁ እንዲሁም ወዲያውኑ እንደሚረሱት ይሰማን ይሆናል። ለይሖዋ ስንል ስለምናከናውነው ሥራስ ምን ማለት ይቻላል? አድናቂ የሆነው አምላካችን፣ እሱን ለማገልገል ስንል በሙሉ ልባችን የምናከናውነውን ሥራ በፍጹም አይረሳም። ባጋጠመን የጤና እክል ምክንያት ማከናወን የምንችለው ነገር የተገደበ ቢሆንም እንኳ ይሖዋ አይተወንም።—ዕብ 6:10
ይሖዋ አይረሳም የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦
-
ወንድም ሂብሽማን በተለያዩ የአገልግሎት ዘርፎች ይሖዋን በትጋት ያገለገለው እንዴት ነው?
-
ወንድም ሂብሽማን፣ ባለቤቱ ከሞተች እንዲሁም ዕድሜው በመግፋቱ ምክንያት አቅሙ ከተገደበ በኋላም ይሖዋ እሱን እንዳልረሳው ያሳየው እንዴት ነው?
-
ወንድም ሂብሽማን በሙሉ ጊዜ አገልግሎት ያሳለፈው ሕይወት በበረከት የተሞላ ነው ሊባል የሚችለው ለምንድን ነው?—ምሳሌ 10:22