ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት
በድፍረት፣ በቁርጠኝነትና በቅንዓት እርምጃ ወስዷል
ይሖዋ ለኢዩ የክፉውን ንጉሥ የአክዓብን ቤት እንዲያጠፋ ተልእኮ ሰጠው (2ነገ 9:6, 7፤ w11 11/15 3 አን. 2)
ኢዩ ወዲያውኑ ይሖዋን በመታዘዝ ንጉሥ ኢዮራምን (የአክዓብን ልጅ) እና ንግሥት ኤልዛቤልን (የአክዓብን ሚስት) ገደላቸው (2ነገ 9:22-24, 30-33፤ w11 11/15 4 አን. 2-3፤ “‘የአክዓብም ቤት በጠቅላላ ይጠፋል’—2ነገ 9:8” የሚለውን ሰንጠረዥ ተመልከት)
ኢዩ በድፍረት፣ በቁርጠኝነትና በቅንዓት የተሰጠውን ተልእኮ ፈጸመ (2ነገ 10:17፤ w11 11/15 5 አን. 3-4)
ራስህን እንዲህ ብለህ ጠይቅ፦ ‘በማቴዎስ 28:19, 20 ላይ ያለውን ተልእኮ በምወጣበት ወቅት የኢዩን ምሳሌ መከተል የምችለው እንዴት ነው?’