ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት
የሥልጣን ጥመኛ የሆነች ክፉ ሴት ከቅጣት አላመለጠችም
ጎቶልያ በይሁዳ ላይ መንገሥ ስለፈለገች የንጉሣውያኑን ቤተሰብ በሙሉ ገደለች (2ነገ 11:1፤ lfb 128 አን. 1-2፤ “‘የአክዓብም ቤት በጠቅላላ ይጠፋል’—2ነገ 9:8” የሚለውን ሰንጠረዥ ተመልከት)
የሆሼባ የዙፋኑ ወራሽ የሆነውን ኢዮዓስን ደበቀችው (2ነገ 11:2, 3)
ሊቀ ካህናቱ ዮዳሄ ኢዮዓስን አነገሠው፤ ክፉዋን ጎቶልያንም አስገደላት፤ ከአክዓብ ቤት የቀረችው የመጨረሻዋ ሰው እሷ ሳትሆን አትቀርም (2ነገ 11:12-16፤ lfb 128 አን. 3-4)
ለማሰላሰል የሚረዳ ጥያቄ፦ ይህ ዘገባ የምሳሌ 11:21ን እና የመክብብ 8:12, 13ን እውነተኝነት የሚያሳየው እንዴት ነው?