ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት
“የአክዓብም ቤት በጠቅላላ ይጠፋል”—2ነገ 9:8
የይሁዳ መንግሥት
ኢዮሳፍጥ ነገሠ
911 ዓ.ዓ. ገደማ፦ ኢዮራም (የኢዮሳፍጥ ልጅ፤ የአክዓብና የኤልዛቤል ልጅ የሆነችው የጎቶልያ ባል) ገዢ ሆነ
906 ዓ.ዓ. ገደማ፦ አካዝያስ (የአክዓብና የኤልዛቤል የልጅ ልጅ) ነገሠ
905 ዓ.ዓ. ገደማ፦ ጎቶልያ የንጉሣውያኑን ቤተሰብ በሙሉ በመግደል ሥልጣን ተቆናጠጠች። የልጅ ልጇ የሆነው ኢዮዓስ ብቻ ተረፈ፤ ከዚያም ሊቀ ካህናቱ ዮዳሄ ከእሷ ደብቆ አቆየው።—2ነገ 11:1-3
898 ዓ.ዓ.፦ ኢዮዓስ ነገሠ። ንግሥት ጎቶልያ በሊቀ ካህናቱ በዮዳሄ ተገደለች።—2ነገ 11:4-16
የእስራኤል መንግሥት
920 ዓ.ዓ. ገደማ፦ አካዝያስ (የአክዓብና የኤልዛቤል ልጅ) ነገሠ
917 ዓ.ዓ. ገደማ፦ ኢዮራም (የአክዓብና የኤልዛቤል ልጅ) ነገሠ
905 ዓ.ዓ. ገደማ፦ ኢዩ የእስራኤልን ንጉሥ ኢዮራምንና ወንድሞቹን፣ የኢዮራምን እናት ኤልዛቤልን እንዲሁም የይሁዳን ንጉሥ አካዝያስንና ወንድሞቹን ገደላቸው።—2ነገ 9:14–10:17
904 ዓ.ዓ. ገደማ፦ ኢዩ ንጉሥ ሆኖ መግዛት ጀመረ