ክርስቲያናዊ ሕይወት
በአስተሳሰብ ንጹሕ አቋምን መጠበቅ
ንጹሕ አቋማችንን እንደምንጠብቅ የምናሳየው በምንናገረውና በምናደርገው ነገር ብቻ ሳይሆን በምናስበው ነገር ጭምር ነው። (መዝ 19:14) መጽሐፍ ቅዱስ እውነት የሆነውን፣ ቁም ነገር ያለበትን፣ ጽድቅ የሆነውን፣ ንጹሕ የሆነውን፣ ተወዳጅ የሆነውን፣ በመልካም የሚነሳውን፣ በጎ የሆነውንና ምስጋና የሚገባውን ነገር ሁሉ እንድናስብ የሚመክረን ለዚህ ነው። (ፊልጵ 4:8) እርግጥ ነው፣ መጥፎ ሐሳብ ወደ አእምሯችን ጨርሶ እንዳይገባ መከላከል አንችልም። ሆኖም ራሳችንን መግዛታችን መጥፎ ሐሳቦችን አውጥተን በምትኩ ጥሩ ሐሳቦች ማስገባት እንድንችል ይረዳናል። በአስተሳሰባችን ንጹሕ አቋማችንን መጠበቃችን በድርጊታችንም ንጹሕ አቋማችንን እንድንጠብቅ ይረዳናል።—ማር 7:21-23
ከእያንዳንዱ ጥቅስ በታች፣ ልናስወግድ የሚገባንን አስተሳሰብ ጻፍ፦