በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ክርስቲያናዊ ሕይወት

ላተረፍነው መልካም ስም እኔ እያበረከትኩ ያለሁት አስተዋጽኦ

ላተረፍነው መልካም ስም እኔ እያበረከትኩ ያለሁት አስተዋጽኦ

ሰዎች የይሖዋ ምሥክሮች የሚያሳዩትን ምግባር በትኩረት ይመለከታሉ። (1ቆሮ 4:9) ‘ንግግሬና ድርጊቴ ለይሖዋ ክብር ያመጣል?’ ብለን ራሳችንን ልንጠይቅ እንችላለን። (1ጴጥ 2:12) የይሖዋ ምሥክሮች ለበርካታ ዓመታት ያተረፉትን መልካም ስም ማጉደፍ እንደማንፈልግ የታወቀ ነው።—መክ 10:1

ክርስቲያን እንደመሆንህ መጠን በቀጣዮቹ ሁኔታዎች ሥር ምን ማድረግ እንዳለብህና የትኛው የመጽሐፍ ቅዱስ መሠረታዊ ሥርዓት ሊረዳህ እንደሚችል ጻፍ፦

  • አንድ የማያምን ሰው ተበሳጭቶ ሲጮኽብህ

  • ልብስህ፣ መኪናህ ወይም ቤትህ ሲዝረከረክ

  • በአካባቢህ ያለ አንድ ሕግ ኢፍትሐዊ ወይም ለመታዘዝ ከባድ እንደሆነ ሲሰማህ

በጽሑፍ ዝግጅት ክፍል ውስጥ የሚሠሩት ምርምር የሚያደርጉ ወንድሞችና እህቶች ላተረፍነው መልካም ስም አስተዋጽኦ የሚያደርጉት እንዴት ነው?

እውነትን መውደድና ከፍ አድርጎ ማየት የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተለውን ጥያቄ ለመመለስ ሞክር፦

ድርጅቱ ትክክለኛ መረጃ ለማስተላለፍ ከሚያደርገው ጥረት ጋር በተያያዘ አንተን የሚያስደንቅህ ምንድን ነው?