በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ክርስቲያናዊ ሕይወት

ወላጆች—ልጆቻችሁ ይሖዋን ማስደሰት የሚችሉት እንዴት እንደሆነ አስተምሯቸው

ወላጆች—ልጆቻችሁ ይሖዋን ማስደሰት የሚችሉት እንዴት እንደሆነ አስተምሯቸው

ልጆች በይሖዋ ፊት በጣም ውድ ናቸው። ይሖዋ፣ የሚያደርጉትን መንፈሳዊ እድገትና ጽናታቸውን በትኩረት ይመለከታል። (1ሳሙ 2:26፤ ሉቃስ 2:52) በጣም ትናንሽ ልጆችም እንኳ ጥሩ ጠባይ በማሳየት የይሖዋን ልብ ደስ ሊያሰኙት ይችላሉ። (ምሳሌ 27:11) ይሖዋ በድርጅቱ አማካኝነት ወላጆች ልጆቻቸው እሱን እንዲወዱትና እንዲታዘዙት ለማሠልጠን ሊጠቀሙባቸው የሚችሉ ግሩም መሣሪያዎችን አዘጋጅቷል።

ልጆች—መጽናታችሁ የይሖዋን ልብ ደስ ያሰኛል! የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦

  • ባለፉት ዓመታት ውስጥ ይሖዋ ልጆችን ለማሠልጠን ምን እርዳታና መመሪያ አዘጋጅቷል?

  • በአሁኑ ጊዜ ወላጆች ሊጠቀሙባቸው የሚችሉ ምን መሣሪያዎች አሉ?

  • ልጅ ከሆንክ ይሖዋ ካዘጋጃቸው ዝግጅቶች መካከል አንተን የጠቀመህ የትኛው ነው? እንዲህ ብለህ የመለስከው ለምንድን ነው?