በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ክርስቲያናዊ ሕይወት

“የተወሰነ ገንዘብ ያስቀምጥ”

“የተወሰነ ገንዘብ ያስቀምጥ”

የፈቃደኝነት መዋጮ፣ ትዝ ሲለን ብቻ የምናደርገው ነገር መሆን የለበትም። ከዚህ ይልቅ ሐዋርያው ጳውሎስ እንዳሳሰበው በቋሚነት ‘የተወሰነ ገንዘብ ማስቀመጥ’ ይኖርብናል። (1ቆሮ 16:2) በመንፈስ መሪነት የተሰጠውን ይህን ምክር መከተላችን ንጹሑን አምልኮ ለመደገፍና ደስታ ለማግኘት ያስችለናል። የምናደርገው መዋጮ ለእኛ የቱንም ያህል ጥቂት መስሎ ቢታየን፣ ይሖዋ ባሉን ውድ ነገሮች እሱን ለማክበር ያለንን ፍላጎት በእጅጉ ያደንቃል።—ምሳሌ 3:9

የተወሰነ ገንዘብ ስላስቀመጣችሁ እናመሰግናችኋለን የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦

  • መዋጮ የምናደርገውን ገንዘብ አስቀድመን ማቀዳችን ምን ጥቅሞች አሉት?

  • አንዳንዶች ‘የተወሰነ ገንዘብ ለማስቀመጥ’ የትኞቹን ዘዴዎች ይጠቀማሉ?