ከታኅሣሥ 16-22
መዝሙር 119:57-120
መዝሙር 129 እና ጸሎት | የመግቢያ ሐሳብ (1 ደቂቃ)
1. መከራን በጽናት መቋቋም የሚቻለው እንዴት ነው?
(10 ደቂቃ)
የአምላክን ቃል ማንበባችሁንና ማጥናታችሁን ቀጥሉ (መዝ 119:61፤ w06 6/15 20 አን. 2፤ w00 12/1 14 አን. 3)
መከራው እንዲያጠራችሁ ፍቀዱ (መዝ 119:71፤ w06 9/1 14 አን. 4)
ማጽናኛ ለማግኘት ወደ ይሖዋ ዘወር በሉ (መዝ 119:76፤ w17.07 13 አን. 3, 5)
ራስህን እንዲህ ብለህ ጠይቅ፦ ‘ይሖዋ ያጋጠሙኝን መከራዎች በጽናት ለመቋቋም የረዳኝ በየትኞቹ መንገዶች ነው?’
2. መንፈሳዊ ዕንቁዎች
(10 ደቂቃ)
-
መዝ 119:96—የዚህ ጥቅስ ትርጉም ምን ሊሆን ይችላል? (w06 9/1 14 አን. 5)
-
ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ምን መንፈሳዊ ዕንቁዎች አግኝታችኋል?
3. የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ
(4 ደቂቃ) መዝ 119:57-80 (th ጥናት 12)
4. ውይይት መጀመር
(3 ደቂቃ) ከቤት ወደ ቤት። ለቤቱ ባለቤት ድረ ገጻችንን አሳየው፤ ከዚያም የjw.org የአድራሻ ካርድ ስጠው። (lmd ምዕራፍ 2 ነጥብ 5)
5. ተመላልሶ መጠየቅ
(4 ደቂቃ) መደበኛ ያልሆነ ምሥክርነት። ግለሰቡን በቀጣዩ የሕዝብ ንግግር ላይ እንዲገኝ ጋብዘው። በስብሰባ አዳራሻችን ውስጥ ምን ይከናወናል? የተባለውን ቪዲዮ ተጠቀም። (lmd ምዕራፍ 8 ነጥብ 3)
6. እምነታችንን ማብራራት
(5 ደቂቃ) ሠርቶ ማሳያ። ijwbq 157—ጭብጥ፦ መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ተፈጥሮ አደጋዎች ምን ይላል? (lmd ምዕራፍ 3 ነጥብ 3)
መዝሙር 128
7. ይሖዋ እንድንጸና ይረዳናል
(15 ደቂቃ) ውይይት።
ክርስቲያናዊ ጽናት፣ ተስፋ ሳይቆርጡ አስቸጋሪ ሁኔታዎችን የመቋቋም ችሎታ ነው። ፈተና እያለም ጽኑ አቋም መያዝን፣ ትክክለኛውን አመለካከት ማዳበርንና ብሩህ ተስፋ መሰነቅን ያካትታል። ጽናት ካለን አስቸጋሪ ሁኔታ ሲያጋጥመን ከክርስትና ጎዳና ‘ወደኋላ አናፈገፍግም’ ወይም ለይሖዋ የምናቀርበውን አገልግሎት አንቀንስም። (ዕብ 10:36-39) ይሖዋ ፈተናዎችን በጽናት እንድንቋቋም ሊረዳን ይፈልጋል።—ዕብ 13:6
ከእያንዳንዱ ጥቅስ ሥር ይሖዋ ለመጽናት የሚረዳን እንዴት እንደሆነ ጻፍ።
በመከራ ውስጥ ላሉት አጥብቃችሁ ጸልዩ የተባለውን ቪዲዮ አጫውት። ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ጠይቅ፦
-
በፈተና ውስጥ ስላሉ ወንድሞቻችን ወቅታዊ መረጃ ለማግኘት jw.orgን መጠቀም የምንችለው እንዴት ነው?
-
ወላጆች ልጆቻቸውን ለሌሎች እንዲጸልዩ ማሠልጠን የሚችሉት እንዴት ነው? ይህስ ምን ጥቅም አለው?
-
ይሖዋ የእምነት አጋሮቻችንን እንዲጸኑ እንዲረዳቸው መጸለያችን አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?
-
ለሌሎች መጸለያችን የሚያጋጥሙንን ፈተናዎች በጽናት ለመቋቋም የሚረዳን እንዴት ነው?
8. የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት
(30 ደቂቃ) bt ምዕ. 19 አን. 14-20፣ በገጽ 152 ላይ ያለው ሣጥን