በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ከታኅሣሥ 23-29

መዝሙር 119:121-176

ከታኅሣሥ 23-29

መዝሙር 31 እና ጸሎት | የመግቢያ ሐሳብ (1 ደቂቃ)

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት

1. ከአላስፈላጊ የስሜት ሥቃይ ራሳችንን መጠበቅ

(10 ደቂቃ)

የአምላክን ትእዛዛት ውደዱ (መዝ 119:127w18.06 17 አን. 5-6)

መጥፎ ድርጊትን ጥሉ (መዝ 119:128w93 4/15 17 አን. 12)

ይሖዋን በመስማት “ተሞክሮ የሌላቸው” ሰዎች ከሚሠሩት ስህተት ተጠበቁ (መዝ 119:130, 133፤ ምሳሌ 22:3)

ራስህን እንዲህ ብለህ ጠይቅ፦ ‘የአምላክን ትእዛዛት በመውደድ ወይም መጥፎ ድርጊትን በመጥላት ረገድ የትኞቹን ማሻሻያዎች ማድረግ ያስፈልገኛል?’

2. መንፈሳዊ ዕንቁዎች

(10 ደቂቃ)

  • መዝ 119:160—ከዚህ ጥቅስ አንጻር ስለ ምን ነገር እርግጠኞች ልንሆን ይገባል? (w23.01 2 አን. 2)

  • ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ምን መንፈሳዊ ዕንቁዎች አግኝታችኋል?

3. የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ

በአገልግሎት ውጤታማ ለመሆን ተጣጣር

4. ውይይት መጀመር

(3 ደቂቃ) ከቤት ወደ ቤት። (lmd ምዕራፍ 1 ነጥብ 5)

5. ተመላልሶ መጠየቅ

(4 ደቂቃ) ከቤት ወደ ቤት። ግለሰቡ ትኩረቱን ሊስብ የሚችል መረጃ ከ​jw.org ላይ እንዴት ማግኘት እንደሚችል አሳየው። (lmd ምዕራፍ 8 ነጥብ 3)

6. ደቀ መዛሙርት ማድረግ

(5 ደቂቃ) በጉባኤ ስብሰባዎች ላይ አዘውትሮ ከማይገኝ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ጋር የሚደረግ ውይይት። (lmd ምዕራፍ 12 ነጥብ 4)

ክርስቲያናዊ ሕይወት

መዝሙር 121

7. ገንዘብ ለአላስፈላጊ ሥቃይ እንዲዳርጋችሁ አትፍቀዱ

(15 ደቂቃ) ውይይት።

የገንዘብ ፍቅራቸውን ለማርካት የሚጣጣሩ ሰዎች “ሁለንተናቸውን በብዙ ሥቃይ ወግተዋል።” (1ጢሞ 6:9, 10) ገንዘብን የምንወድ ከሆነና ገንዘብ ማሳደድን የሕይወታችን ዓላማ አድርገን ከተነሳን ለብዙ አላስፈላጊ ሥቃይ እንዳረጋለን፤ ለምሳሌ፦

  • ከይሖዋ ጋር የጠበቀ ዝምድና መመሥረት አንችልም።—ማቴ 6:24

  • መቼም ቢሆን አንረካም።—መክ 5:10

  • እንደ ውሸት፣ ስርቆት እና ማጭበርበር ላሉ የሥነ ምግባር ፈተናዎች ይበልጥ እንጋለጣለን። (ምሳሌ 28:20) ለፈተናዎቹ እጅ ከሰጠን ደግሞ በበደለኝነት ስሜት እንዋጣለን፤ መልካም ስማችን ይበላሻል፤ እንዲሁም የአምላክን ሞገስ እናጣለን

ዕብራውያን 13:5ን አንብብ። ከዚያም እንዲህ ብለህ ጠይቅ፦

  • የስሜት ሥቃይ እንዳይደርስብን ለገንዘብ ምን ዓይነት አመለካከት ሊኖረን ይገባል? ለምንስ?

የገንዘብ ፍቅር ባይኖረንም እንኳ ገንዘባችንን በአግባቡ ካልያዝን ለስሜት ሥቃይ እንዳረጋለን።

የገንዘብ አያያዝ የተባለውን የነጭ ሰሌዳ አኒሜሽን አጫውት። ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ጠይቅ፦

  • በጀት ማውጣት ያለብን ለምንድን ነው? ይህን ማድረግ የምንችለውስ እንዴት ነው?

  • የተወሰነ ገንዘብ መቆጠባችን ጠቃሚ የሆነው ለምንድን ነው?

  • አላስፈላጊ ዕዳ ውስጥ አለመግባት ጥበብ የሆነው ለምንድን ነው?

8. የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የመደምደሚያ ሐሳብ (3 ደቂቃ) | መዝሙር 101 እና ጸሎት