በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ከታኅሣሥ 30, 2024–ጥር 5, 2025

መዝሙር 120–126

ከታኅሣሥ 30, 2024–ጥር 5, 2025

መዝሙር 144 እና ጸሎት | የመግቢያ ሐሳብ (1 ደቂቃ)

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት

ወደ አገራቸው የተመለሱት እስራኤላውያን ይሖዋ ልፋታቸውን ስለባረከላቸው በደስታ ሲያጭዱ

1. በእንባ ዘርተው በእልልታ አጨዱ

(10 ደቂቃ)

እስራኤላውያን ከባቢሎን ነፃ ወጥተው ንጹሑን አምልኮ መልሰው ማቋቋም በመቻላቸው ተደስተው ነበር (መዝ 126:1-3)

ወደ ይሁዳ የተመለሱት ሰዎች ከሥራው ክብደት የተነሳ አልቅሰው ሊሆን ይችላል (መዝ 126:5w04 6/1 16 አን. 10)

ሕዝቡ በመጽናታቸው ተባርከዋል (መዝ 126:6w21.11 24 አን. 17፤ w01 7/15 18-19 አን. 13-14፤ ሥዕሉን ተመልከት)

ለማሰላሰል የሚረዳ ጥያቄ፦ በአርማጌዶን ጦርነት አማካኝነት ከዚህ አሮጌ ዓለም ከተገላገልን በኋላ በታላቁ የመልሶ ግንባታ ሥራ ወቅት የትኞቹ ተፈታታኝ ሁኔታዎች ያጋጥሙናል? የትኞቹን በረከቶችስ እናገኛለን?

2. መንፈሳዊ ዕንቁዎች

(10 ደቂቃ)

  • መዝ 124:2-5—ይሖዋ ለእስራኤል ብሔር እንዳደረገው ለእኛም አካላዊ ጥበቃ ያደርግልናል ብለን መጠበቅ እንችላለን? (cl 73 አን. 15)

  • ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ምን መንፈሳዊ ዕንቁዎች አግኝታችኋል?

3. የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ

በአገልግሎት ውጤታማ ለመሆን ተጣጣር

4. ውይይት መጀመር

(3 ደቂቃ) የአደባባይ ምሥክርነት። (lmd ምዕራፍ 3 ነጥብ 5)

5. ተመላልሶ መጠየቅ

(4 ደቂቃ) ከቤት ወደ ቤት። ባለፈው ውይይታችሁ ወቅት ግለሰቡ በመጽሐፍ ቅዱስ ማመን እንደሚከብደው ነግሮህ ነበር። (lmd ምዕራፍ 9 ነጥብ 5)

6. ደቀ መዛሙርት ማድረግ

ክርስቲያናዊ ሕይወት

መዝሙር 155

7. አምላክ በሰጣቸው ተስፋዎች ተደሰቱ

(15 ደቂቃ) ውይይት።

ይሖዋ በባቢሎን በግዞት ለነበሩ ሕዝቦቹ የገባውን ቃል ፈጽሟል። ነፃ አውጥቷቸዋል፤ እንዲሁም በመንፈሳዊ ፈውሷቸዋል። (ኢሳ 33:24) ከሁኔታዎች መረዳት እንደሚቻለው፣ ሕዝቡ በግዞት በነበሩበት ወቅት በምድሪቱ ላይ ከተበራከቱት አንበሶችና ሌሎች አራዊት እነሱንም ሆነ የቤት እንስሶቻቸውን ጠብቋቸዋል። (ኢሳ 65:25) በገዛ ቤታቸው ውስጥ መኖርና ራሳቸው የተከሉትን ወይን ፍሬ መብላት ችለዋል። (ኢሳ 65:21) አምላክ ሥራቸውን ባርኮላቸዋል፤ ረጅም ዕድሜም ኖረዋል።—ኢሳ 65:22, 23

Waterfall: Maridav/stock.adobe.com; mountains: AndreyArmyagov/stock.adobe.com

አምላክ ስለ ሰላም በሰጣቸው ተስፋዎች ተደሰቱ—ተቀንጭቦ የተወሰደ የተባለውን ቪዲዮ አጫውት። ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ጠይቅ፦

  • እነዚህ ትንቢቶች በመንፈሳዊ ሁኔታ ፍጻሜያቸውን ሲያገኙ እያየን ያለነው እንዴት ነው?

  • በአዲሱ ዓለም በላቀ ሁኔታ ፍጻሜያቸውን የሚያገኙት እንዴት ነው?

  • በተለይ የትኛው ተስፋ ሲፈጸም ማየት ትፈልጋላችሁ?

8. የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የመደምደሚያ ሐሳብ (3 ደቂቃ) | መዝሙር 58 እና ጸሎት