በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ከኅዳር 18-24

መዝሙር 107–108

ከኅዳር 18-24

መዝሙር 7 እና ጸሎት | የመግቢያ ሐሳብ (1 ደቂቃ)

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት

1. “ይሖዋ ጥሩ ስለሆነ ምስጋና አቅርቡለት”

(10 ደቂቃ)

ይሖዋ እስራኤላውያንን ከባቢሎን እንደታደጋቸው ሁሉ እኛንም ከሰይጣን ዓለም ታድጎናል (መዝ 107:1, 2፤ ቆላ 1:13, 14)

ለይሖዋ አመስጋኝ መሆናችን በጉባኤ ውስጥ እንድናወድሰው ያነሳሳናል (መዝ 107:31, 32w07 4/15 20 አን. 2)

ይሖዋ ፍቅሩን በገለጸባቸው መንገዶች ላይ ማሰላሰላችን አመስጋኝ ልብ ለማዳበር ይረዳናል (መዝ 107:43w15 1/15 9 አን. 4)

2. መንፈሳዊ ዕንቁዎች

(10 ደቂቃ)

  • መዝ 108:9—ሞዓብ የአምላክ “መታጠቢያ ገንዳ” ተብሎ መጠራቱ ምን ሊያመለክት ይችላል? (it-2 420 አን. 4)

  • ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ምን መንፈሳዊ ዕንቁዎች አግኝታችኋል?

3. የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ

በአገልግሎት ውጤታማ ለመሆን ተጣጣር

4. ውይይት መጀመር

(3 ደቂቃ) መደበኛ ያልሆነ ምሥክርነት። (lmd ምዕራፍ 1 ነጥብ 4)

5. ተመላልሶ መጠየቅ

(4 ደቂቃ) መደበኛ ያልሆነ ምሥክርነት። የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ስለምንሰጥበት ዝግጅት ለግለሰቡ ንገረው፤ እንዲሁም የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት የአድራሻ ካርድ ስጠው። (lmd ምዕራፍ 9 ነጥብ 3)

6. ንግግር

(5 ደቂቃ) ijwyp 90—ጭብጥ፦ አሉታዊ አመለካከትን ማስወገድ የምችለው እንዴት ነው? (th ጥናት 14)

ክርስቲያናዊ ሕይወት

መዝሙር 46

7. ይሖዋን በመዝሙር እናመሰግነዋለን

(15 ደቂቃ) ውይይት።

ይሖዋ በፍርሃት የተዋጡትን እስራኤላውያን ኃያል ከሆነው የግብፅ ሠራዊት በቀይ ባሕር ካዳናቸው በኋላ ሕዝቡ በአመስጋኝነት ስሜት ተገፋፍተው መዝሙር ዘመሩ። (ዘፀ 15:1-19) ይህን አዲስ መዝሙር ግንባር ቀደም ሆነው የዘመሩት ወንዶቹ ናቸው። (ዘፀ 15:21) ኢየሱስና የጥንቶቹ ክርስቲያኖችም ለአምላክ የምስጋና መዝሙር ዘምረዋል። (ማቴ 26:30፤ ቆላ 3:16) እኛም በጉባኤ፣ በወረዳ እና በክልል ስብሰባዎች ላይ በመዘመር ለይሖዋ ያለንን አመስጋኝነት እንገልጻለን። ለምሳሌ አሁን የዘመርነው “ይሖዋ እናመሰግንሃለን” የሚለው መዝሙር ከ1966 አንስቶ በስብሰባዎቻችን ላይ ሲዘመር ቆይቷል።

በአንዳንድ ባሕሎች ውስጥ ወንዶች ሰው ፊት መዘመር ያሳፍራቸው ይሆናል። ሌሎች ደግሞ ድምፃቸው ጥሩ እንዳልሆነ ስለሚሰማቸው ከመዘመር ወደኋላ ይላሉ። ይሁንና በስብሰባዎቻችን ላይ መዘመር የአምልኳችን ክፍል እንደሆነ ማስታወስ ይኖርብናል። የይሖዋ ድርጅት ግሩም ሆነው የተቀናበሩ መዝሙሮችን ለማዘጋጀትና ለእያንዳንዱ ስብሰባ ተስማሚ የሆነ መዝሙር ለመምረጥ ተግቶ ይሠራል። ከዚህ አንጻር ከእኛ የሚጠበቀው ነገር ቀላል ነው፤ የሚጠበቅብን ድምፃችንን አስተባብረን ለሰማዩ አባታችን ያለንን ልባዊ ፍቅርና አድናቆት መግለጽ ብቻ ነው።

ታሪካችን—ከየት ወዴት?—የመዝሙር ስጦታ፣ ክፍል 2 የተባለውን ቪዲዮ አጫውት ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ጠይቅ፦

  • በ1944 ምን ተከናውኗል?

  • በሳይቤሪያ ያሉ ወንድሞቻችን ለመንግሥቱ መዝሙሮች ያላቸውን አድናቆት የገለጹት እንዴት ነው?

  • የይሖዋ ምሥክሮች ለመዝሙር ትልቅ ቦታ የሚሰጡት ለምንድን ነው?

8. የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የመደምደሚያ ሐሳብ (3 ደቂቃ) | መዝሙር 73 እና ጸሎት