በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ክርስቲያናዊ ሕይወት

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ያስተምረናል? የተባለውን መጽሐፍ እንዴት ልንጠቀምበት እንችላለን?

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ያስተምረናል? የተባለውን መጽሐፍ እንዴት ልንጠቀምበት እንችላለን?

ምን ያስተምረናል? (እንግሊዝኛ) እና የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት የተባሉት መጻሕፍት ተመሳሳይ ይዘት አላቸው። ለማስተማር በምንጠቀምባቸው ሁለቱም መጻሕፍት ላይ ትምህርቶቹ የተቀመጡበት ቅደም ተከተል ተመሳሳይ ነው። ሆኖም ምን ያስተምረናል? የተባለው መጽሐፍ ቀለል ያለ አገላለጽና ማብራሪያ ይጠቀማል። ይህ መጽሐፍ፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት የተባለውን መጽሐፍ መረዳት የሚከብዳቸውን ሰዎች ለመርዳት ታስቦ የተዘጋጀ ነው። ምን ያስተምረናል? የተባለው መጽሐፍ ተጨማሪ ክፍል የለውም፤ ከዚህ ይልቅ አንዳንድ አገላለጾችንና ሐሳቦችን ቀለል ባለ መንገድ የሚያብራራ ተጨማሪ ሐሳብ የሚል ክፍል አለው። ምዕራፎቹ የመግቢያ ጥያቄዎች ወይም የክለሳ ሣጥን የላቸውም። ከዚህ ይልቅ በምዕራፎቹ መደምደሚያ ላይ በዋናው ጽሑፍ ውስጥ የተብራሩትን እውነቶች ጠቅለል አድርጎ የሚገልጽ ክለሳ ይገኛል። የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት እንደተባለው መጽሐፍ ሁሉ ምን ያስተምረናል? የተባለውን መጽሐፍም በማንኛውም ጊዜ (በወሩ የሚበረከተው ጽሑፍ ባይሆንም እንኳ) ልናበረክተው እንችላለን። ምን ያስተምረናል? የተባለው መጽሐፍ ያሉትን ለየት ያሉ ገጽታዎች የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ስንመራ እንዴት ልንጠቀምባቸው እንችላለን?

ክለሳ፦ አብዛኞቹን ሰዎች የምናስጠናው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት በተባለው መጽሐፍ ላይ ያሉትን አንቀጾች አንብበን ጥያቄዎቹን በመጠየቅ ነው። ነገር ግን አንዳንድ ሰዎች ቋንቋውን መረዳት ይከብዳቸው ወይም በደንብ ማንበብ አይችሉ ይሆናል። በዚህ ጊዜ ምን ያስተምረናል? የተባለውን መጽሐፍ መጠቀም ይቻላል። ከዚያም የምዕራፎቹን ክለሳ እንደ ዋና ማስጠኛ መጠቀምና ግለሰቡ ምዕራፉን በግሉ እንዲያነበው ማበረታታት እንችላለን። ክለሳው ላይ የሚገኘውን እያንዳንዱን የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ለማስጠናት በአብዛኛው 15 ደቂቃ ሊፈጅ ይችላል። በምዕራፉ ውስጥ ያሉት ዝርዝር ሐሳቦች በክለሳው ላይ ስለማይገኙ አስጠኚው የጥናቱን ሁኔታ ግምት ውስጥ በማስገባት በሚገባ መዘጋጀት ይኖርበታል። አስጠኚው ጥናቱን የሚመራው በዋናው ጽሑፍ ተጠቅሞ ከሆነ ደግሞ ክለሳውን ጥናቱን ለመከለስ ሊጠቀምበት ይችላል።

ተጨማሪ ሐሳብ፦ በዚህ ክፍል ውስጥ የሚገኙት አገላለጾችና ሐሳቦች የተቀመጡት በዋናው ጽሑፍ ውስጥ በሚገኙበት ቅደም ተከተል ነው። አስጠኚው ተጨማሪ ሐሳቡን በጥናቱ ወቅት ይወያዩበት እንደሆነና እንዳልሆነ ይወስናል።