በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | መክብብ 7-12

“በወጣትነትህ ጊዜ ታላቁን ፈጣሪህን አስብ”

“በወጣትነትህ ጊዜ ታላቁን ፈጣሪህን አስብ”

በወጣትነታችሁ፣ ያላችሁን ችሎታ ታላቁን ፈጣሪያችሁን ለማገልገል በመጠቀም እሱን ማሰብ ትችላላችሁ

12:1, 13

  • ብዙ ወጣቶች፣ ተፈታታኝ ኃላፊነቶችን ለመወጣት የሚያስችል ጤንነትና ጉልበት አላቸው

  • ወጣቶች፣ በዕድሜ ገፍተው አቅማቸው ሳይገደብ በፊት ጊዜያቸውንና ጉልበታቸውን አምላክን ለማገልገል መጠቀም አለባቸው

ሰለሞን ቅኔያዊ አነጋገር በመጠቀም ከዕድሜ መግፋት ጋር ተያይዘው ስለሚመጡት ችግሮች ገልጿል

12:2-7

  • ቁጥር 3፦ ‘በመስኮት የሚያዩ ወይዛዝርት ይጨልምባቸዋል’

    የዓይን መድከም

  • ቁጥር 4፦ ‘ሴቶች ልጆች ዝግ ባለ ድምፅ ይዘምራሉ’

    የመስማት ችሎታ መዳከም

  • ቁጥር 5 (የግርጌ ማስታወሻ)፦ ‘ከእንጆሪ ጋር የሚመሳሰለው ተክል’ ፍሬ ይፈነዳል

    የምግብ ፍላጎት መቀነስ