በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ክርስቲያናዊ ሕይወት

ወጣቶች፣ ‘በትልቁ በር’ ለመግባት አታመንቱ

ወጣቶች፣ ‘በትልቁ በር’ ለመግባት አታመንቱ

ወጣት ሳለን፣ ሁልጊዜ ወጣት ሆነን እንደምንኖርና በዕድሜ መግፋት ምክንያት በሚመጡት ‘አስጨናቂ ዘመናት’ ውስጥ እንደማናልፍ ይሰማን ይሆናል። (መክ 12:1) ወጣት ከሆንክ፣ በሙሉ ጊዜ አገልግሎት እንደ መካፈል የመሰሉ መንፈሳዊ ግቦችን ማሳካት የምትችልበት ጊዜ እንዳለህና የትም እንደማያመልጥህ ይሰማሃል?

ወጣቶችን ጨምሮ ሁላችንም “ያልተጠበቁ ክስተቶች” ያጋጥሙናል። (መክ 9:11) ‘ሕይወታችን ነገ ምን እንደሚሆን እንኳ አናውቅም።’ (ያዕ 4:14) ስለዚህ አስገዳጅ ሁኔታ እስከሌለ ድረስ መንፈሳዊ ግቦችን ለመከታተል ዛሬ ነገ አትበል። በተከፈተልህ “ትልቅ የሥራ በር” ለመግባት አታመንታ። (1ቆሮ 16:9) ይህን በማድረግህ በፍጹም አትቆጭም።

ልታወጣቸው የምትችላቸው አንዳንድ መንፈሳዊ ግቦች፦

  • በሌላ ቋንቋ መመሥከር

  • የአቅኚነት አገልግሎት

  • በቲኦክራሲያዊ ትምህርት ቤቶች መካፈል

  • የግንባታ አገልግሎት

  • የቤቴል አገልግሎት

  • የወረዳ ሥራ

የአንተን መንፈሳዊ ግቦች ጥቀስ።