በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | ምሳሌ 27-31

መጽሐፍ ቅዱስ ባለሙያ ሚስትን የሚገልጽበት መንገድ

መጽሐፍ ቅዱስ ባለሙያ ሚስትን የሚገልጽበት መንገድ

ምሳሌ ምዕራፍ 31 የንጉሥ ልሙኤል እናት ለልጇ የተናገረችውን ከፍተኛ ቁም ነገር ያዘለ መልእክት ይዟል። የሰጠችው ጥበብ የሚንጸባረቅበት ምክር፣ አንዲት ባለሙያ ሚስት ተለይታ የምትታወቅባቸውን ነገሮች እንዲገነዘብ ረድቶታል።

ባለሙያ ሚስት እምነት የሚጣልባት ናት

31:10-12

  • ቤተሰቡን የሚመለከቱ ውሳኔዎች ሲኖሩ ለባሏ እንደምትገዛ በሚያሳይ መንገድ ጠቃሚ ሐሳብ ትሰጣለች

  • ባሏ ጥበብ የሚንጸባረቅባቸው ውሳኔዎች እንደምታደርግ ስለሚተማመንባት ለእያንዳንዱ ጉዳይ የእሱን ፈቃድ ማግኘት እንዳለባት አይሰማውም

ባለሙያ ሚስት ታታሪ ናት

31:13-27

  • የቤተሰቧ አባላት ንጹሕና ጥሩ አለባበስ እንዲኖራቸውና በደንብ እንዲመገቡ ለማድረግ ያላትን አብቃቅታ ለመጠቀም እንዲሁም በአቅሟ ለመኖር ትጥራለች

  • ቤተሰቧን ለመንከባከብ ቀን ከሌት ተግታ ትሠራለች

ባለሙያ ሚስት መንፈሳዊ ናት

31:30

  • አምላክን ትፈራለች፤ እንዲሁም ከእሱ ጋር የጠበቀ ዝምድና አላት