በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የአቀራረብ ናሙናዎች

የአቀራረብ ናሙናዎች

መጠበቂያ ግንብ

ጥያቄ፦ አንድ ሰው ‘ሰማይ ምን ዓይነት ቦታ ነው?’ ቢልህ ምን ብለህ ትመልሳለህ?

ጥቅስ፦ ዮሐ 8:23

አበርክት፦ ይህ የመጠበቂያ ግንብ እትም፣ ኢየሱስና አባቱ ሰማይን በተመለከተ ምን እንደገለጹ ያብራራል።

እውነትን አስተምሩ

ጥያቄ፦ ይህ የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢት በዛሬው ጊዜ በዓለማችን ላይ የሚታየውን ሁኔታ በትክክል ይገልጻል ቢባል አትስማማም?

ጥቅስ፦ 2ጢሞ 3:1-5

እውነት፦ መጽሐፍ ቅዱስ ስለ መጨረሻው ዘመን የሚናገረው ትንቢት በአሁኑ ጊዜ እየተፈጸመ ነው፤ ስለዚህ ወደፊት የተሻለ ጊዜ እንደሚመጣ የሚናገረው ትንቢትም ፍጻሜውን እንደሚያገኝ እርግጠኞች መሆን እንችላለን።

መጽሐፍ ቅዱስን መማር የሚኖርብን ለምንድን ነው? (ቪዲዮ)

መግቢያ፦ ሰዎች፣ በአእምሯቸው ውስጥ ለሚጉላሉ ጥያቄዎች አጥጋቢ መልስ ማግኘት የሚችሉት ከየት እንደሆነ የሚጠቁም አጭር ቪዲዮ እያሳየናቸው ነው። [ቪዲዮውን አጫውት።]

አበርክት፦ ይህ መጽሐፍ፣ አምላክ በዓለም ላይ ያሉትን ችግሮች የሚያስወግድበትን መንገድ አስመልክቶ መጽሐፍ ቅዱስ ምን እንደሚል ይናገራል። [የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት የተባለውን መጽሐፍ አበርክት።]

የራስህን መግቢያ አዘጋጅ

ከላይ የተጠቀሱትን ምሳሌዎች እንደ ናሙና አድርገህ በመጠቀም በመስክ አገልግሎት ላይ የምትጠቀምበት የራስህን አቀራረብ አዘጋጅ።