በማላዊ በክልል ስብሰባ ላይ የተገኙ ሰዎች አመሻሹ ላይ አብረው JW ብሮድካስቲንግ ሲያዩ

የክርስቲያናዊ ሕይወትና አገልግሎት ስብሰባ አስተዋጽኦ ኅዳር 2019

የውይይት ናሙናዎች

የሕይወት ዓላማ ምን እንደሆነ እንዲሁም አምላክ ለወደፊቱ ጊዜ ስለሰጠን ተስፋ ለመወያየት የሚረዱ የውይይት ናሙናዎች።

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት

ዓለምንም ሆነ በዓለም ውስጥ ያሉትን ነገሮች አትውደዱ

ዓለምና በውስጡ ያሉት ነገሮች ከይሖዋ እንዳያርቁን መጠንቀቅ የምንችለው እንዴት ነው?

ክርስቲያናዊ ሕይወት

ሠርጋችሁን ስታዘጋጁ ይህ ዓለም ተጽዕኖ እንዳያሳድርባችሁ ተጠንቀቁ

ሠርጋቸውን እያቀዱ ያሉ ጥንዶች ሕሊናቸውን በማይረብሽና ለቁጭት በማይዳርግ መንገድ ሠርጋቸውን እንዲያዘጋጁ የሚረዷቸው አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ መሠረታዊ ሥርዓቶች የትኞቹ ናቸው?

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት

እውነት ውስጥ ለመቆየት ብርቱ ተጋድሎ ማድረግ አለብን

‘ለእምነት ብርቱ ተጋድሎ’ ማድረግ የምንችለው እንዴት ነው?

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት

‘ሥራህን አውቃለሁ’

ኢየሱስ በጉባኤዎች ውስጥ የሚከናወነውን ነገር በሙሉ ያውቃል እንዲሁም በሽማግሌዎች አካል ላይ ሙሉ ቁጥጥር አለው።

ክርስቲያናዊ ሕይወት

ይሖዋ ምን እንደሚያስፈልገን ያውቃል

በክልል ስብሰባ ላይ ስንገኝ የሚያስፈልገንን ትምህርት እንዳገኘን የሚሰማን ለምንድን ነው? የሳምንቱ መሃል ስብሰባችን አበረታችና ጠቃሚ የሆነው ለምንድን ነው?

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት

የአራቱ ፈረሰኞች ግልቢያ

በዛሬው ጊዜ በራእይ መጽሐፍ ላይ የተጠቀሱት አራቱ ምሳሌያዊ ፈረሰኞች ሲጋልቡ እያየን ነው። እነዚህ ፈረሰኞች ምን ያመለክታሉ?

ክርስቲያናዊ ሕይወት

ይሖዋ በደስታ የሚሰጠውን ሰው ይወዳል

በምንኖርበት አገርም ሆነ በዓለም ዙሪያ የሚካሄደውን የይሖዋ ምሥክሮች እንቅስቃሴ ለመደገፍ መዋጮ ማድረግ የምንችለው እንዴት ነው?