በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | 2 ዮሐንስ 1-13፤ 3 ዮሐንስ 1-14ይሁዳ 1-25

እውነት ውስጥ ለመቆየት ብርቱ ተጋድሎ ማድረግ አለብን

እውነት ውስጥ ለመቆየት ብርቱ ተጋድሎ ማድረግ አለብን

ይሁዳ 3

ኢየሱስ “በጠባቡ በር ለመግባት ከፍተኛ ተጋድሎ አድርጉ” የሚል ማሳሰቢያ ሰጥቷል። (ሉቃስ 13:24) ኢየሱስ የተናገረው ሐሳብ በአምላክ ዘንድ ተቀባይነት ለማግኘት ብርቱ ትግል ማድረግ እንደሚያስፈልገን ይጠቁማል። የኢየሱስ ወንድም ይሁዳም ‘ለእምነት ብርቱ ተጋድሎ አድርጉ’ በማለት በመንፈስ መሪነት ጽፏል። የሚከተሉትን ነገሮች ለማድረግ ከፍተኛ ጥረት ያስፈልጋል፦

  • ከፆታ ብልግና ለመራቅ።—ይሁዳ 6, 7

  • በኃላፊነት ቦታ ላይ ያሉትን ለማክበር።—ይሁዳ 8, 9

  • “እጅግ ቅዱስ” በሆኑት ክርስቲያናዊ ትምህርቶች ላይ ያለንን እምነት ለማጠናከር።—ይሁዳ 20, 21