ክርስቲያናዊ ሕይወት
ይሖዋ ምን እንደሚያስፈልገን ያውቃል
ታማኝና ልባም ባሪያ “በተገቢው ጊዜ” ምግብ ይሰጠናል። ይህም ታማኝና ልባም ባሪያን የሚመራው ይሖዋ፣ በመንፈሳዊ ምን እንደሚያስፈልገን እንደሚያውቅ ይጠቁማል። (ማቴ 24:45) የክልል ስብሰባዎቻችንና በሳምንቱ መሃል የምናደርገው ስብሰባ ይህን ከሚያሳዩ በርካታ ምሳሌዎች ውስጥ ጥቂቶቹ ናቸው።
የትምህርት ኮሚቴ የ2017 ሪፖርት የተባለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦
-
ወቅታዊ ለሆኑት የክልል ስብሰባዎቻችን ሊመሰገን የሚገባው ማን ነው? ለምንስ?
-
አንድን የክልል ስብሰባ ማዘጋጀት የሚጀመረው ስብሰባው ከመደረጉ ከምን ያህል ጊዜ በፊት ነው?
-
የክልል ስብሰባው ርዕሰ ጉዳይ የሚመረጠው እንዴት ነው?
-
የክልል ስብሰባዎችን የማዘጋጀቱ ሥራ ምን ነገሮችን ያካትታል?
-
የሳምንቱ መሃል ስብሰባ የተዘጋጀበት መንገድ ከጊልያድ የሥልጠና መርሕ ጋር የሚመሳሰለው እንዴት ነው?
-
የስብሰባውን አስተዋጽኦ ለማዘጋጀት የተለያዩ ዲፓርትመንቶች ተቀናጅተው የሚሠሩት እንዴት ነው?
ይሖዋ ለሚያደርግልን መንፈሳዊ ዝግጅቶች በግለሰብ ደረጃ ምን አመለካከት አለህ?