በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ክርስቲያናዊ ሕይወት

ይሖዋ በደስታ የሚሰጠውን ሰው ይወዳል

ይሖዋ በደስታ የሚሰጠውን ሰው ይወዳል

ሁለተኛ ቆሮንቶስ 9:7 “አምላክ በደስታ የሚሰጠውን ሰው ስለሚወድ እያንዳንዱ ሰው ቅር እያለው ወይም ተገዶ ሳይሆን በልቡ ያሰበውን ይስጥ” ይላል። በዛሬው ጊዜ፣ በአገራችንም ሆነ በዓለም ዙሪያ የሚካሄደውን የይሖዋ ምሥክሮች እንቅስቃሴ ለመደገፍ በኢንተርኔት መዋጮ ማድረግ የምንችልባቸው አመቺ አማራጮች አሉ።

በኤሌክትሮኒክ መሣሪያዎች መዋጮ ማድረግ የሚቻለው እንዴት ነው? የተባለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦

  • በአገራችን መዋጮ ማድረግ ስለምንችልበት መንገድ ለማወቅ፣ ከመዋጮ ጋር የተያያዙ መረጃዎች የያዘውን ገጽ ማግኘት የምንችለው እንዴት ነው?

  • አንዳንዶች በኤሌክትሮኒክ መሣሪያዎች መዋጮ በማድረጋቸው ምን ጥቅም አግኝተዋል?

  • መዋጮ ማድረግ የሚቻልባቸው አንዳንድ መንገዶች የትኞቹ ናቸው?

  • በኤሌክትሮኒክ መሣሪያዎች መዋጮ ማድረግ የሚቻለው እንዴት እንደሆነ ግልጽ ካልሆነልን ምን ማድረግ እንችላለን?