በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ክርስቲያናዊ ሕይወት

ሠርጋችሁን ስታዘጋጁ ይህ ዓለም ተጽዕኖ እንዳያሳድርባችሁ ተጠንቀቁ

ሠርጋችሁን ስታዘጋጁ ይህ ዓለም ተጽዕኖ እንዳያሳድርባችሁ ተጠንቀቁ

ሠርጋቸውን እያቀዱ ያሉ ክርስቲያን ጥንዶች ብዙ ውሳኔዎችን ማድረግ ይጠበቅባቸዋል። በአካባቢያቸው በተለመደው መሠረት ድል ያለ ድግስ እንዲደግሱ ተጽዕኖ ሊደረግባቸው ይችላል። ጓደኞቻቸውና የቤተሰባቸው አባላት በቅን ልቦና ተነሳስተው የራሳቸውን ሐሳብ ሊጭኑባቸው ይሞክሩ ይሆናል። ታዲያ ሠርጋቸውን እያቀዱ ያሉ ጥንዶች ሕሊናቸውን በማይረብሽና ለቁጭት በማይዳርግ መንገድ ሠርጋቸውን እንዲያዘጋጁ የሚረዷቸው አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ መሠረታዊ ሥርዓቶች የትኞቹ ናቸው?

ይሖዋን የሚያስከብር የሠርግ ሥነ ሥርዓት የተባለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦

  • ከዚህ በታች የተዘረዘሩት የመጽሐፍ ቅዱስ መሠረታዊ ሥርዓቶች ኒክንና ጁሊያናን የረዷቸው እንዴት ነው?

  • እጮኛሞች በመንፈሳዊ የጎለመሰን አንድ ወንድም የሠርጉ “አሳዳሪ” አድርገው መምረጥ ያለባቸው ለምንድን ነው?—ዮሐ 2:9, 10

  • ኒክና ጁሊያና ከሠርጋቸው ጋር በተያያዘ ላደረጓቸው የግል ምርጫዎች ምክንያት የሆኗቸው ነገሮች ምንድን ናቸው?

  • ከሠርጉ ሥነ ሥርዓትና ከድግሱ ጋር በተያያዘ የመጨረሻውን ውሳኔ የማድረግ ኃላፊነት ያለበት ማን ነው?—w06 10/15 25-26 አን. 10