በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | ዘሌዋውያን 4–5

ለይሖዋ ምርጣችሁን ስጡት

ለይሖዋ ምርጣችሁን ስጡት

5:5-7, 11

ድህነት የትኛውንም እስራኤላዊ ከይሖዋ ጋር ሰላማዊ ግንኙነት እንዳይመሠርት ሊያግደው አይችልም ነበር። በጣም ድሃ የሆኑ እስራኤላውያን እንኳ ምርጣቸው እስከሆነ ድረስ በይሖዋ ዘንድ ተቀባይነት ያለው መባ ማቅረብ ይችሉ ነበር። ዱቄት መባ አድርገው ማቅረብ ይችሉ የነበረ ቢሆንም ዱቄቱ ለተከበረ እንግዳ የሚቀርበው ዓይነት “የላመ” ዱቄት መሆን ነበረበት። (ዘፍ 18:6) በዛሬው ጊዜም የግል ሁኔታችን መስጠት የምንችለውን ነገር ቢገድበውም እንኳ ምርጣችን እስከሆነ ድረስ ይሖዋ የምናቀርበውን “የውዳሴ መሥዋዕት” ይቀበላል።—ዕብ 13:15

በጤና ችግር ወይም በአቅም ማጣት ምክንያት የቀድሞውን ያህል መሥራት ባትችሉ ይህ ሐሳብ ሊያበረታታችሁ የሚችለው እንዴት ነው?