በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ከኅዳር 2-8

ዘፀአት 39–40

ከኅዳር 2-8

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት

  • ሙሴ የተሰጠውን መመሪያ በጥንቃቄ ተከትሏል”፦ (10 ደቂቃ)

    • ዘፀ 39:32—ሙሴ ከማደሪያ ድንኳኑ አሠራር ጋር በተያያዘ ይሖዋ የሰጠውን መመሪያ በጥንቃቄ ተከትሏል (w11 9/15 27 አን. 13)

    • ዘፀ 39:43—ሙሴ የማደሪያ ድንኳኑ ከተሠራ በኋላ በደንብ በመቃኘት በትክክል መሠራቱን አረጋግጧል

    • ዘፀ 40:1, 2, 16—ሙሴ የማደሪያ ድንኳኑን በይሖዋ መመሪያ መሠረት ተክሏል (w05 7/15 26 አን. 3)

  • መንፈሳዊ ዕንቁዎችን በምርምር ማግኘት፦ (10 ደቂቃ)

    • ዘፀ 39:34—እስራኤላውያን ለማደሪያ ድንኳኑ የአቆስጣ ቆዳ ያገኙት ከየት ሊሆን ይችላል? (it-2 884 አን. 3)

    • ዘፀ 40:34—ደመናው የመገናኛ ድንኳኑን መሸፈኑ ምን ያመለክታል? (w15 7/15 21 አን. 1)

    • ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ይሖዋን፣ የመስክ አገልግሎትን ወይም ሌሎች ነገሮችን በተመለከተ ምን መንፈሳዊ ዕንቁዎች አግኝታችኋል?

  • የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች) ዘፀ 39:1-21 (th ጥናት 5)

በአገልግሎት ውጤታማ ለመሆን ተጣጣር

  • መመሥከር—ቪዲዮ፦ (4 ደቂቃ) በውይይት የሚቀርብ። ቪዲዮውን አጫውት። ውይይቱ ቆም ሲል ቪዲዮውን አቁመህ በቪዲዮው ላይ ያሉትን ጥያቄዎች ለአድማጮች አቅርብ። የምናነጋግረው ሰው ፖለቲካዊ ጉዳዮችን ወይም አወዛጋቢ የሆኑ ማኅበራዊ ጉዳዮችን ካነሳ የገለልተኝነት አቋማችንን መጠበቅ የምንችለው እንዴት እንደሆነ ተወያዩ።

  • መመሥከር፦ (3 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች) በውይይት ናሙናው ጀምር። የቤቱ ባለቤት ስለ አንድ የፖለቲካ ተወዳዳሪ ወይም ፖለቲካዊ ጉዳይ ያለህን አመለካከት በተመለከተ ለሚያነሳው ጥያቄ መልስ ስጥ። (th ጥናት 12)

  • ንግግር፦ (5 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች) w16.04 29 አን. 8-10—ጭብጥ፦ በንግግራችንና በአስተሳሰባችን ክርስቲያናዊ የገለልተኝነት አቋማችንን መጠበቅ የምንችለው እንዴት ነው? (th ጥናት 14)

ክርስቲያናዊ ሕይወት

  • መዝሙር 123

  • በማስተዋል አዳምጡ (ማቴ 13:16)፦ (15 ደቂቃ) ቪዲዮውን አጫውት። ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ጠይቅ፦ በማስተዋል ማዳመጥ የሚያስፈልገን ለምንድን ነው? የማርቆስ 4:23, 24 ትርጉም ምንድን ነው? በዕብራውያን 2:1 ላይ የሚገኘውን ሐሳብ በምሳሌ ማስረዳት የሚቻለው እንዴት ነው? በማስተዋል እንደምናዳምጥ የምናሳየው እንዴት ነው?

  • የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦ (30 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች) jy ምዕ. 137 እና 138

  • የመደምደሚያ ሐሳብ (3 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)

  • መዝሙር 69 እና ጸሎት