የይሖዋን በረከት የሚያሳይ ማስረጃ
ይሖዋ የአሮንና የዘሮቹ የክህነት ሥርዓት እንደተቋቋመ አዲሶቹ ካህናት ያቀረቡትን የመጀመሪያ የሚቃጠል መባ፣ እሳት ከእሱ ፊት ወጥቶ እንዲበላው አድርጓል። ይህም ዝግጅቱን ይሖዋ እንደተቀበለውና እንደሚደግፈው ያሳያል። ይሖዋ በዚህ መንገድ በቦታው የተሰበሰበው መላው ብሔር ለክህነት ሥርዓቱ የተሟላ ድጋፍ እንዲሰጥ አበረታቷል። በዛሬው ጊዜም ይሖዋ ክብር የተላበሰው ኢየሱስ ታላቅ ሊቀ ካህናት እንዲሆን ሾሞታል። (ዕብ 9:11, 12) በ1919 ኢየሱስ በመንፈስ የተቀቡ ጥቂት ወንዶችን ያቀፈ ቡድን “ታማኝና ልባም ባሪያ” ሆኖ እንዲያገለግል ሾሟል። (ማቴ 24:45) ታማኙ ባሪያ የይሖዋ በረከት፣ ድጋፍና ሞገስ እንዳለው የሚያሳይ ምን ማስረጃ አለ?
-
ከፍተኛ ስደት ቢኖርም ታማኙ ባሪያ መንፈሳዊ ምግብ ማቅረቡን ቀጥሏል
-
በትንቢት በተነገረው መሠረት ምሥራቹ “በመላው ምድር” እየተሰበከ ነው።—ማቴ 24:14
ለታማኝና ልባም ባሪያ ሙሉ ድጋፍ መስጠት የምንችለው እንዴት ነው?