በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ክርስቲያናዊ ሕይወት

“ሁለት ትናንሽ ሳንቲሞች” ያላቸው ዋጋ

“ሁለት ትናንሽ ሳንቲሞች” ያላቸው ዋጋ

መበለቲቱ የሰጠችው መዋጮ ቀለል ያለ ምግብ ለመግዛት እንኳ የሚበቃ አልነበረም። (w08 3/1 12 አን. 1-3⁠ን ተመልከት።) ያም ቢሆን ያደረገችው መዋጮ ለይሖዋ አምልኮ ያላትን ጥልቅ ፍቅርና አድናቆት የሚያሳይ ነበር። በዚህም የተነሳ መዋጮዋ በሰማይ በሚኖረው አባቷ በይሖዋ ዘንድ ከፍተኛ ዋጋ ነበረው።—ማር 12:43

“ለይሖዋ የሚሰጥ ስጦታ” የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦

  • የምናደርገው መዋጮ የትኞቹን እንቅስቃሴዎች ለመደገፍ ይውላል?

  • የምናደርገው መዋጮ መጠኑ ትንሽ ቢመስልም ትልቅ ዋጋ አለው የምንለው ለምንድን ነው?

  • በምንኖርበት አካባቢ ስላሉት የመዋጮ አማራጮች ማወቅ የምንችለው እንዴት ነው?—“ ኢንተርኔት ላይ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት” የሚለውን ሣጥን ተመልከት