ነሐሴ 1-7
መዝሙር 87-91
መዝሙር 49 እና ጸሎት
መግቢያ ሐሳብ (3 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት
“ከልዑሉ አምላክ ሚስጥራዊ ቦታ አትውጡ”፦ (10 ደቂቃ)
መዝ 91:1, 2—የይሖዋ “ሚስጥራዊ ቦታ” መንፈሳዊ ጥበቃ ያስገኛል (w10 2/15 26-27 አን. 10-11)
መዝ 91:3—ሰይጣን ልክ እንደ አንድ ወፍ አዳኝ ሊያጠምደን ይሞክራል (w07 10/1 26-30 አን. 1-18)
መዝ 91:9-14—ይሖዋ መጠጊያችን ነው (w10 1/15 10-11 አን. 13-14፤ w01 11/15 19-20 አን. 13-19)
መንፈሳዊ ዕንቁዎችን በምርምር ማግኘት፦ (8 ደቂቃ)
መዝ 89:34-37—በዚህ ጥቅስ ላይ የተጠቀሰው የትኛው ቃል ኪዳን ነው? ይሖዋ ቃል ኪዳኑ አስተማማኝ መሆኑን ለመግለጽ ምን ምሳሌ ተጠቅሟል? (w14 10/15 10 አን. 14፤ w07 7/15 32 አን. 3-4)
መዝ 90:10, 12—‘ጥበበኛ ልብ ማግኘት እንችል ዘንድ ዕድሜያችንን መቁጠር’ የምንችለው እንዴት ነው? (w06 7/15 13 አን. 4፤ w01 11/15 13 አን. 19)
የዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ስለ ይሖዋ ምን ያስተምረኛል?
የዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ለመስክ አገልግሎት ሊጠቅሙኝ የሚችሉ ምን ነጥቦች ይዟል?
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች) መዝ 90:1-17
በአገልግሎት ውጤታማ ለመሆን ተጣጣር
የዚህን ወር መግቢያዎች ተዘጋጅ፦ (15 ደቂቃ) በውይይት የሚቀርብ። እያንዳንዱን የአቀራረብ ናሙና ቪዲዮ አጫውት፤ ከዚያም ጎላ ባሉ ነጥቦች ላይ ተወያዩ። አስፋፊዎች የራሳቸውን መግቢያ እንዲያዘጋጁ አበረታታ።
ክርስቲያናዊ ሕይወት
ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት፦ (5 ደቂቃ)
“በአገልግሎት ረገድ ክህሎታችንን ማዳበር—የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች ራሳቸውን እንዲወስኑና እንዲጠመቁ መርዳት”፦ (10 ደቂቃ) በውይይት የሚቀርብ። ጥናቱ ራሱን እንዲወስንና እንዲጠመቅ ለረዳ አንድ አስፋፊ የሚከተሉትን ጥያቄዎች በመጠቀም ቃለ ምልልስ አድርግ። ጥናትህ ይሖዋን ከልቡ እንዲወድ ለመርዳት ጥረት ያደረግከው እንዴት ነው? ጥናትህ መንፈሳዊ ግቦች ላይ እንዲደርስ የረዳኸው እንዴት ነው?
የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦ (30 ደቂቃ) ia ምዕ. 16 አን. 16-29 እና “አንድ ትንቢት ፍጻሜውን አገኘ” የሚለው ሣጥንና የምዕራፉ ክለሳ
ክለሳና የቀጣዩ ሳምንት ማስተዋወቂያ (3 ደቂቃ)
መዝሙር 137 እና ጸሎት