ክርስቲያናዊ ሕይወት
በአገልግሎት ረገድ ክህሎታችንን ማዳበር—የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች ራሳቸውን እንዲወስኑና እንዲጠመቁ መርዳት
አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች በይሖዋ ዘንድ ተቀባይነት ማግኘት ከፈለጉ ራሳቸውን ለአምላክ መወሰንና መጠመቅ አለባቸው። (1ጴጥ 3:21) ራሳቸውን ለአምላክ ሲወስኑ ከገቡት ቃል ጋር ተስማምተው የሚኖሩ ሰዎች መንፈሳዊ ጥበቃ ያገኛሉ። (መዝ 91:1, 2) አንድ ክርስቲያን ራሱን የሚወስነው ለሰዎች፣ ለአንድ ሥራ ወይም ድርጅት ሳይሆን ለይሖዋ ነው። ስለዚህ ተማሪዎቹ ለአምላክ ጥልቅ ፍቅርና አድናቆት ማዳበር ይኖርባቸዋል።—ሮም 14:7, 8
ይህን ማድረግ የሚቻለው እንዴት ነው?
-
በጥናቱ ወቅት ከሚማሩት ነገር ስለ ይሖዋ ምን መገንዘብ እንደቻሉ ተወያዩ። መጽሐፍ ቅዱስን በየቀኑ ማንበብና “ዘወትር” መጸለይ ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ ጎላ አድርጋችሁ ግለጹ።—1ተሰ 5:17፤ ያዕ 4:8
-
ጥናታችሁ ራሱን የመወሰንና የመጠመቅ ግብ እንዲያወጣ አበረታቱት። በተጨማሪም ወደዚያ የሚያደርሱ ሌሎች ግቦችን ለምሳሌ በስብሰባ ላይ መልስ የመስጠት ወይም ለጎረቤቶቹና ለሥራ ባልደረቦቹ የመመሥከር ግብ እንዲያወጣ እርዱት። ይሖዋ እሱን እንዲያገለግል ማንንም ሰው እንደማያስገድድ አስታውሱ። ራስን መወሰን እያንዳንዱ ሰው በግሉ የሚያደርገው ውሳኔ ነው።—ዘዳ 30:19, 20
-
ጥናታችሁ ይሖዋን ለማስደሰትና ለመጠመቅ የሚያስፈልገውን ብቃት ለማሟላት አስፈላጊ ለውጦችን የማድረግ ፍላጎት እንዲያድርበት እርዱት። (ምሳሌ 27:11) አንዳንድ ባሕርያትና ልማዶች ሥር የሰደዱ ሊሆኑ ይችላሉ፤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናታችሁ አሮጌውን ስብዕና አውልቆ እንዲጥልና አዲሱን ስብዕና እንዲለብስ ቀጣይ የሆነ እርዳታ መስጠት ሊያስፈልግ ይችላል። (ኤፌ 4:22-24) “መጽሐፍ ቅዱስ የሰዎችን ሕይወት ይለውጣል” በሚለው ተከታታይ ርዕስ ላይ የወጡ አንዳንድ ሐሳቦችን አካፍሉት
-
ይሖዋን በማገልገል ያገኛችኋቸውን አስደሳች ተሞክሮዎች ንገሩት።—ኢሳ 48:17, 18